30
Apr 2016
በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አድሮ የዋለባት ዕለት በመሆኗ «ቀዳሚት ሥዑር » ትሰኛለች፡፡ ቀዳሚት ሥዑር የተባለችው በዓመት አንድ ቀን ስለ ሚጾምባት ነው፡፡ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያም ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንስተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ። አልቀመሱም ፡፡ አምላካቸው በመቃብር ስላደረ ዕለቷን ሞቱን በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም ውለዋል። ከቅዱሳን ሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን በመጾምና በመጸለይ ዕለቷ እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆች የተቻላቸው ከዓርብ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ ቀምሰው ቅዳሜን በመጾም/ በማክፈል ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ ለምን......
Read More