Monthly Archives: September 2016


29
Sep 2016
የመስቀል ደመራ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በድምቀት ተከበረ

በፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተማ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን አደባባይ. /ሜዳ / ላይ በተካሄደው የደመራ ሥነ ሥርዓት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ፣ የሄልሲንኪ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሪትቫ ቪልያነን ፣ የደብሩ ዲያቆናት ፣ የሄልሲንኪ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት ዲያቆናት እና ምእመናን ፣ ጥንግ ድርብ የለበሱ የደብሩ መዘምራን፣ ሕጻናት፣ ከሄልሲንኪና ከአጎራባች ከተሞች የመጡ ምእመናን፣ የባህል እና የሌሎች ተቋማት ሓላፊዋች ፣ጋዜጠኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ከ 17፡30 – 20፡30 በተካሄደ የመስቀል ደመራ ሥነ ሥርዓት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። ሥነ......

Read More


24
Sep 2016
የመስቀል ደመራ ለመጀመሪያ ጊዜ በሂልሲንኪ ሊከበር ነው

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ የመስቀል ደመራን በዓል በሄልሲንኪ ከተማ የዮሐንስ ቤ/ክ አጠገብ በሚገኘው (korkeavuorenkatu 12) አደባባይ/ሜዳ/ ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ከ17፡30– 20፡30 ፣ የደመራ ሥነ ሥርዓት በማከናወን እንደሚያከብር ተገለጸ። የደመራ ሥነ ሥርዓቱ የደብሩ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን፣ ሕጻናት፣ በሄልሲንኪና አጎራባች ከተሞች የሚገኙ ምእመናን፤ ተጋባዥ ካህናት፣ ዲያቆናት ፣ የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሓላፊዎች ፣ የከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት እና ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እንደሚከናወን ታውቋል፡፡ የመስቀል ደመራ በዓል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአይሁድ አማካኝነት ተቀብሮ ከነበረበት ቦታ የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት የሆነቸው ንግሥት ዕሌኒ ፣ ደመራ......

Read More