አቡነ ዘበሰማያት
አባታችን ሆይ (ግዕዝ፦ አቡነ ዘበሰማያት) ወይም የጌታ ጸሎት በማቴዎስ ወንጌል 6 እና በሉቃስ ወንጌል 11 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ነው። በግዕዝ አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻእ መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሀበነ ዮም ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመን ሐሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት አላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኩሉ አኩይ እስመ ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም አሜን:: በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ ድንግል በሕሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ እመ እዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ ቡርክት አንቲ እም አንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርስኪ ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ ጸልዪ ወሰአሊ ምሕረተ ኀበ ፍቁር ወልድኪ አየሱስ ክርስቶስ ከመ ይስረይ ለነ ኀጣውኢነ አሜን:: በአማርኛ አባታችን ሆይ! በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንድንል አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት ያንተ ናትና ኅይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን! እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ፥ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ። በሀሳብሽ ድንግል ነሽ ፤ በሥጋሽም ድንግል ነሽ አሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታንና ምሕረትን ለምኝልን ኃጢአታችንን ይቅር ይለን ዘነድ ለዘለዓለሙ አሜን።
Recent Sermons
ዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብር ኄር
April 14, 2021
ዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ምኲራብ
April 12, 2021
ዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት
April 12, 2021
ቃለሕይወት ያሰማልን