24
Nov 2017
ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡......
Read More
07
Apr 2016
በቀሲስ ብርሃኑ ጎበና ቤት የሚለው ቃል ወገን፤ ነገድ፤ ዘር፤ ትውልድ፤ ጉባኤ፤ ማኅበር ማለት እንደሆነ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡(ኪ.ወ.ክ ገጽ 268) የያዕቆብ ወገን ቤተ ያዕቆብ (ቤተ እስራኤል)፤የዳዊት ወገን ቤተ ዳዊት እንዲባል በመንፈሳዊና በምሥጥራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ ምእመናንም ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ፤ ቤተ ክርስቶስ (የክርስቶስ ወገን) እንደ ማለት ነው፡፡ ዳሩ ግን በዘመናችን ስምና ግብር ለየቅል ሆነው በተቃራኒ ያሉት ወገኖች ሳይቀሩ ስሙን መጠሪያ አድርገው አናስተውላለን፤ ዘመናችን አማናዊቱ ቤተ ክርስቲያን ስምዋን ወስደው በሚጠሩ አስመሳዮች የተወረረችበት ወቅት በመሆኑ እውነተኛዋን ለይቶ ማወቅ ግድ ይላል፡፡ እንዲት ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ክርስቲያን ዘክርስቶስ የሚያሰኛት በ381 ዓ.ም በቁስጥንጥንያ የተሰበሰቡት......
Read More
07
Apr 2016
እግዚአብሔር አምላክ ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣው ከተፈጠረበት ሥርዓት ጋር ነው። የዓለም ተፈጥሮም ያለ ሥርዓት ትርጉም የለውም። ፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔርን ከሚያደንቅበት ነገር አንዱ የተሰጠውን ሥርዓት ጠብቆ መጓዙ ነው። ወንዞች ወደ ዝቅተኛ ስፍራ ይፈስሳሉ፣ አራዊት በሌሊት ይወጣሉ፣ ሰዎች ተግባራቸውን በቀን ያከናውናሉ፣ ፀሐይ በምሥራቅ ትወጣለች። ይህ ሁሉ የሚያስተምረን ሥርዓት ከጥንተ ፍጥረት ጀምሮ የነበረና ወደፊትም የሚቀጥል መሆኑን ነው። መዝ ፩፻፫፡ ፮-፳፭። ሥርዓት ሠርዐ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ስም ነው። ትርጉሙም ደምብ አሠራር ማለት ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ስንል የቤተ ክርስቲያን መገልገያ ደንብ ማለታችን ነው። አምልኮተ እግዚአብሔር የሚከናወንባት ቤተ ክርስቲያን ምስጢራዊና መንፈሳዊ ሥርዓት አላት። መንፈሳዊ......
Read More