21
Jan 2020
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ጥር 11 /አሥራ አንድ የሚከበረው የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በተለየ ሃይማኖታዊ ድምቀት ተከብሯል። የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡን ተከትሎ ዘንድሮ ሥርዓቱን በጠበቀና በደመቀ መልኩ ታቦተ ሕጉ በምእመናን ታጅቦ ከበዓሉ ዋዜማ በሚከበረው የከተራ በዓል ጊዜያዊ ማረፊያው ጉዞ አድርጎል:: ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ድምቀት የተጀመረው የጥምቀት በዓሉ ሌሊቱን በካህናቱ አገልግሎት አድሮ ከሌሊቱ 10 /አሥር ሰዓት/ ጀምሮ የቅዳሴ ሥነ ሥርዓቱ ቀጥሏል። የቅዳሴው ሥርዓት ከተፈፀመ በኋላ ባሕረ ጥምቀቱ ተባርኮ ሕዝበ ክርስቲያኑም ጠበል ተረጭቷል። የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቀሲስ......
Read More
07
Apr 2016
ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ክርስቲያናዊ ትውፊታዋንና ኀይማኖታዊ አስተምህሮዋን ጠብቃ የኖረች ናት ። ከአስተምህሮዋም አንዱና ዋንኛው ምሥጢረ ሥላሴ ነው ። ምሥጢረ ሥላሴ ( የእግዚአብሔር ባሕርይ ) ምሉዕና ስፉሕ ረቂቅና ምጡቅ የሆነ ተመጣጣኝ ምሳሌ የማይገኝለት ቢሆንም ፣ ቅዱሳን ነቢያትና ቅዱሳን ሐዋርያት በመንፈሰ እግዚአብሔር እየተመሩ የጻፏቸውን መጻሕፍተ ብሉያትንና መጻሕፍተ ሐዲሳትን ምስክር በማድረግ አበው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደ አስተማሩን ፣ (በምሳሌ ዘየሐጽጽ) ደካማው አዕምሯችን በሚረዳው ዕኛ በምናውቀው ለሥላሴ ተመጣጣኝ ባልሆነ በአነስተኛ ምሳሌ እየመሰልን የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት በዕርሱ አጋዥነትና ረዳትነት ለመጻፍ እጀምራለሑ ፡፡ ሰውን በአርዓያችንና በአምሳላችን እንፍጠር ነቢይ ሙሴ በጻፈው......
Read More
07
Apr 2016
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረ፤ ያለና የሚኖር አንድ አምላክ መኖሩን ታምናለች፡፡ ይኸውም አንድ አምላክ፤ በአካል፤ በስም፣ በግብር ሦስት፤ በመለኮት አንድ የሆነ አንድ እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን አምና ታሳምናለች፤ ተምራ ታስተምራለች፡፡ ስለ እግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት፤ ፈጣሪነትና መጋቢነት… የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባላት ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ መሰረት ከአምስቱ አእማደ ምሥጢር አንደኛውን ክፍል ምሥጢረ ሥላሴን እንመለከታለን፡፡ ሥላሴ ማለት ሠለሰ ሦስት አደረገ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተወሰደ ሲሆን ትርጓሜውም ሦስት ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ሥሉስ ቅዱስ ማለት ደግሞ ልዩ ሦስት ማለት ነው፡፡ ልዩነቱም የአካል ሦስትነት ካላቸው የህልውና አንድነት ከሌላቸው ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ......
Read More