NewsTicker


29
Sep 2022
የ፳፻፲፭ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በሄልሲንኪ ፊንላንድ በደማቅ ሥነሥርዓት ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ማርያም አቢያተ ክርስቲያን በአንድነት የመስቀልን ደመራ በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት አከበሩ። በዕለቱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ካህናት እና ምእመናን ከመላዋ ፊንላንድ የመጡ በአንድነት በቦታው ተገኝተዋል።በተጨማሪም በክብር እንግድነትም የሂልሲንኪ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሊዮ ዋና ፀሐፊ ቀሲስ ላዛርዩስ ተገኝተው ለሕዝበ ክርስቲያኑ መልእክት አስተላልፈዋል።   በመጨረሻም የሁለቱ አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድና ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ አንገሶም ዕቁባይ ትምህርት ከሰጡ በኋላ ደመራው ተለኩሶ ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ዝማሬ ዘምረው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖአል።...

Read More


21
Aug 2022
የደብረ ታቦር በዓል በሄልሲንኪ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ

በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የደብረ ታቦር በዓል የደብሩ ሕጻናት አዳጊ ልጆች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል ። የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይሜኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት በተለይ በዝርወቱ ዓለም ተወልደው የሚያድጉ ተተኪው ትውልድ የበዓላትን አከባበር እንዲሁም ትውፊታዊውንም ቅብብል በተግባር ያውቁ ዘንድ እንዲያስችል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። ወላጆችም ለዚሁ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብለዋል ። በቀጣይ የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመትም እንዲሁ በደሜቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከበር ጠቁመዋል። በተያያዘ ዜና ነሐሴ 14 /2014 ዓ.ም በታምፔሬ ከተማ በታምፔሬ የሚገኙ የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጽዋዕ ማኅበር አባላት......

Read More


25
Jul 2021
የአገልግሎት ምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ

በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለወ/ሮ አለማች ገብረ ሚካኤል የአገልግሎት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጠ። በሀገረ ፊንላንድ ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ በመንፈሳዊ አገልግሎት በማኅበራዊ አገልግሎት ለሚታውቁት ወ/ሮ አለማች ፣ ሐምሌ ፲፯/፳፻፲፫ ዓ.ም በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት የምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ ። በዕለቱም በመርሐግብሩ የታደሙት ምእመናን ወ/ሮ አለማች በሀገረ ፊንላንድ በስደት ለሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ያዘነውን በማጽናናት ፣ በመጠየቅ የሀገረ ፊንላንድንም ሥርዓተ ሀገሩንም በማለማመድ ከፍተኛ አገልግሎት ማበርከታቸውን ተናግረዋል ። ወ/ሮ አለማች በተለይ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከታላቁ ካህን አባታቸውና ከለጋሷ እናታቸው የወረሱትን በጎ ተግባር ስደቱ ተጽእኖ ሳይፈጥርባቸው ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን......

Read More


17
Jun 2019

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ቅዱሳን አውሮጳ ማዕከል የፊንላንድ ግንኙነት ጣቢያ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት የቆየው መንፈሳዊ ጉባዔ ባለፈው ሳምንት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ልዩ ጉባኤ ተካሄዷል ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር መጋቤ ሐዲስ በሙሉ አስፋው መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርትን ጨምረው በንስሐ ሕይወት እና በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ሰፋ ያለ ትምህርት ሰጥተዋል ። ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ የማኅበረቅዱሳን በአዉሮፖ ማዕከል የፊንላንድ ግንኙነት ጣቢያ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ መንፈሳዊ መዝሙሮች እና ሥነጽሑፍ በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ቀርቧል ። በርካታ......

Read More


16
May 2019
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ያተኮረ ልዩ ዐውደ ጥናት  በሄልሲንኪ ተካሄደ!

በፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በጋራ የተዘጋጀው ልዩ ዐውደ ጥናት ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 3 2011 ዓ.ም (May 11 2019) በፊንላንድ ሄልሲንኪ በሚገኘው ሶፊያ የባህል ማዕከል በርካታ ምእመናን እና ታዳሚዎች በተገኙበት ተካሄዷል :: ለሦስተኛ ጊዜ በተዘጋጀው እና ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥናታዊ ጽሑፎች በአንድ ኢትዮጵያዊ እና በሦስት ፊንላንዳውያን ሙሑራን ቀርቧል ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ገዳማትና ገዳማዊ ሕይወት ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ በቀዳሚነት በዲያቆን አረጋ ጌታነህ ቀርቦ ግንዛቤ አስጨብጧል። ለረጅም ዓመታት የፊንላንድ ሉተራን ቤተክርስቲያን አለቃ የነበሩት ኒሎ ሆንካነን በነገረ ማርያም ዙሪያ በተለይ ማኅሌተ ጽጌን በተመለከተ......

Read More


19
Mar 2019
የሀገረ ስብከት ምሥረታ ተከናወነ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አውሮጳ መንበረ ጵጵስናው ስዊድን ስቶኮሆልም የሆነ ሀገረ ስብከት ተመሠረተ ።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት አሠርተ ዓመታት ያህል በአስተዳደር ተከፍላ ብትቆይም በሐምሌ 2010 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሕደቱ ከተፈጸመ በኋላ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት አውሮጳን ለዐራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል መወሰኑ ይታወቃል ። በዚህ መሠረት በስዊድንና እስካንድንቢያን ሀገሮች እራሱን ችሎ አንድ ሀገረ ስብከት እንዲሆንና በአንጋፋው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እንዲመራ በመወሰን የተነሳ መጋቢት 6 እና 7 /2011 ዓ.ም በመንበረ ጵጵስናው ስቶኮሆልም ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሰብሳቢነት ምሥረታው......

Read More


22
Jan 2019
ከሲኖዶሳዊ አንድነቱ በኋላ የመጀመሪያው የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ በዓል በፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተማ በጋራ ተከበረ

ከሲኖዶሳዊ ዕርቅና ሰላም በኋላ የመጀመሪያው በዓለ ጥምቀት በሰሜን አውሮፓ በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ÷ ጥር 11 ቀን 2011 ዓ.ም በጋራ ተከበረ፡፡ የበዓሉ የአከባበር ሥነ ሥርዐት እና ጸሎተ ቅዳሴው በደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያ አስተዳዳሪ ÷ በመልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱ ፈቃድ እየተመራ ÷ከተለያዩ የፊንላንድ ከተሞች የመጡ ኦርቶዶክሳውያን በተገኙበት በጸሎተ ቅዳሴና በትምህርተ ወንጌል በድምቀት ተከብሯል፡፡ በተዘጋጀው የባሕረ ጥምቀት ሥፍራ ስብሐተ እግዚአብሔር ደርሶ፣በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ዕለቱን የሚያዘክር ወረብ ቀርቦና ከኢትዮጵያ በመጡት መምህር ÷በዲያቆን ታደሰ ወርቁ በዓሉን የተመለከተ ትምህርት ከተሰጠ በኋላ የበዓሉ ፍጻሜ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ ከዚሁ ጋራ......

Read More


24
Sep 2018
በፊንላንድ ሄልሲንኪ ታላቅ የአንድነት እና ሰላም ጉባኤ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ውስጥ በሚገኘው በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 12 – 13 ቀን 2011 ዓ.ም ታላቅ የአንድነት እና ሰላም ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤው ላይም የአውሮፓ አኅጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ቀዳማዊ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ፣ ጥሪ የተደረገላቸው ካህናት፤ ከመላው ፊንላንድ የተሰባሰቡ ምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች  ተገኝተዋል። ጉባኤው ቅዳሜ መስከረም 12 ቀን 2011 ጠዋት በሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት እየተመራ በጸሎተ ቅዳሴ ተጀምሯል። የአንድነት ጉባኤውን ለማድረግ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያትም በቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መከፋፈል ምክንያት ለሁለት ተከፍለው የነበሩትን በፊንላንድ የሚኖሩ ምዕመናን......

Read More


09
Sep 2018
አዲሱ ዓመት (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

አዲሱ ዓመት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡ የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ......

Read More


29
Jul 2018

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ልኡካን አባቶች ረቡዕ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ፤ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ በመጪው መስከረም ለመመለስ ቢያስቡም፣ በጠ/ሚሩ ጥሪ አሳጠሩት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአቀባበል ዐቢይ ኮሚቴ ዝግጅቱን እያጣደፈ ነው፤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ፣ ከ17 በላይ የተሟሉ ማረፊያዎች ተዘጋጁ፤ ይፋዊ የአቀባበል መርሐ ግብሩ፣ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል፤ “ለመቀበል እየተዘጋጀን ነው፤ታላቅ ደስታ ነው፤”/ብፁዕ ዋና ሥ/አስኪያጁ/ †††   የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ አንድነት በአባቶች ዕርቀ ሰላም መመለሱን ተከትሎ፣ ላለፉት 26 ዓመታት በአሜሪካ በስደት የቆዩት 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በመጪው ሳምንት ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ሀገራቸው......

Read More