NewsTicker


01
Jan 2016
የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን የልደታቸው ንግሥ በዓል የፊታችን ቅዳሜ  ይከበራል

+ + + በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። “አእምሩ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሔር በጻድቁ” .መዝ. 4,3 “እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተመሰገነ እወቁ ” መዝ .4፣ 3 የተከበራችሁ ምእመናንና ምእመናት! እግዚአብሔር ቢፈቅድ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን የልደታቸው ንግሥ በዓል የፊታችን ቅዳሜ ታኅሣሥ ፳፫ (Sat Jan 2) በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ይከበራል ። በዕለቱም የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡነ እንጦንስ፣ እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ካህናት እና ዲያቆናት ይገኛሉ።ሥርዓተ ዋዜማው ከምሽት ፭ (23:00) ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል። የሌሊቱም ሥርዓተ ማኃሌት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ምእመናን እና ምእመናት በሚገኙበት ተቁሞ ይታደራል። ሥርዓተ ቅዳሴው በሊቀ ጳጳሱ......

Read More


14
Nov 2015

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በፊንላንድ ለምትኖሩ ሕዝበ ክርስቲያኖች በሙሉ፦ በእግዚአብሔር አምላካችን ቸርነት፣ በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎትና ተራዳኢነት፤  የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ብሎም በፊንላንድ ውስጥ የመጀመሪያው ቋሚ ካህን መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፍቃድ (ቀሲስ) ለመምጣት በዝግጅት ላይ ናቸው። የእግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃዱ ቢሆን አባታችን ቅዳሜ ኅዳር 4 ቀን 2008 ዓ.ም.  (November 14, 2015)  ሄልሲንኪ ይገባሉ።  እግዚአብሔር አምላካችንን እያመሰገንን፤ ለሁላችሁም እንኳን ደስ አለን እንላለን። ለመምህራችንን የእንኳን ደህና መጡ፣በሄልሲንኪ ውስጥና በፊንላድ በተለያዩ ከተሞች ከሚኖሩ ህዝበ ክርስቲያኖች ጋር  የትውውቅ መርሐ ግብር እሁድ ኅዳር 5 ቀን 2008 ዓ.ም. (November 15, 2015) ......

Read More