የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ቋሚ ካህን ነገ ሄልሲንኪ ይገባሉ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በፊንላንድ ለምትኖሩ ሕዝበ ክርስቲያኖች በሙሉ፦
በእግዚአብሔር አምላካችን ቸርነት፣ በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎትና ተራዳኢነት፤  የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ብሎም በፊንላንድ ውስጥ የመጀመሪያው ቋሚ ካህን መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፍቃድ (ቀሲስ) ለመምጣት በዝግጅት ላይ ናቸው። የእግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃዱ ቢሆን አባታችን ቅዳሜ ኅዳር 4 ቀን 2008 ዓ.ም.  (November 14, 2015)  ሄልሲንኪ ይገባሉ።  እግዚአብሔር አምላካችንን እያመሰገንን፤ ለሁላችሁም እንኳን ደስ አለን እንላለን።
ለመምህራችንን የእንኳን ደህና መጡ፣በሄልሲንኪ ውስጥና በፊንላድ በተለያዩ ከተሞች ከሚኖሩ ህዝበ ክርስቲያኖች ጋር  የትውውቅ መርሐ ግብር እሁድ ኅዳር 5 ቀን 2008 ዓ.ም. (November 15, 2015)  ከቀኑ 15፡15 እስከ ምሽቱ 1፡00 ድረስ ተዘጋጅቷል።  ስለዚህ በፊንላንድ የምትኖሩ ክርስቲያኖች በሙሉ በእለቱ በመገኜት አባታችንና መምህራችንን እንኳን ደህና መጡ እንድትሏቸው፤ እንድትተዋወቋቸው በአክብሮት ተጋብዛችኋል።  ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህንን ያደረገልንን አምላካችንን በአንድነት ሆነን እንድናመሰግነው፣ ህያው ቃሉንም እንድንሰማ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
መርሐ ግብር፦
ጠዋት (12፡00 – 5፡00) 
ከንጋቱ 12፡00 – ጠዋቱ 2፡00  ስብሐተ ነግህ
ከጠዋቱ 2፡00 – ቀኑ 5፡00 ቅዳሴ እና ትምህርተ ወንጌል እና መዝሙር
ቦታ፡ Kotikyläntie 5, 02770 Espoo (Espoo Keskus)

ከሰዓት
ከቀኑ 9፡15 – ምሽቱ 1፡00 ትምህርተ ወንጌል፣መዝሙር፣ የአቀባበል መርሐ ግብር
ቦታ፡  Opastinsilta 6A, Helsinki (Pasila)

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
በኢ.ኦ.ተ.ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት
የሄስሊንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *