የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን የልደታቸው ንግሥ በዓል የፊታችን ቅዳሜ ይከበራል

የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን የልደታቸው ንግሥ በዓል የፊታችን ቅዳሜ  ይከበራል

+ + +

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“አእምሩ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሔር በጻድቁ” .መዝ. 4,3
“እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተመሰገነ እወቁ ” መዝ .4፣ 3

የተከበራችሁ ምእመናንና ምእመናት!
እግዚአብሔር ቢፈቅድ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን የልደታቸው ንግሥ በዓል የፊታችን ቅዳሜ ታኅሣሥ ፳፫ (Sat Jan 2) በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ይከበራል ። በዕለቱም የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡነ እንጦንስ፣ እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ካህናት እና ዲያቆናት ይገኛሉ።ሥርዓተ ዋዜማው ከምሽት ፭ (23:00) ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል። የሌሊቱም ሥርዓተ ማኃሌት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ምእመናን እና ምእመናት በሚገኙበት ተቁሞ ይታደራል። ሥርዓተ ቅዳሴው በሊቀ ጳጳሱ እየተመራ በአባቶች ይከናወንና በመጨረሻም በሊቀ ጳጳሱ ምዕዳን እና ጸሎት የበዓለ ንግሡ ፍጻሜ ይሆናል።
ስለዚህ እርስዎም በእነዚህ ዕለታት በቦታው በመገኘትና ላልሰሙት በማሰማት የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። በዓሉ የሚከበርበት ቦታ እና ሰዓት እንደሚከተለዉ ነዉ።

ንግሥ በዓል
ቀን ፦ ዓርብ ታኅሣሥ ፳፪ – ቅዳሜ ፳፫ ቀን ፳፻፰ (Fri Jan 1 – Sat Jan 2 2016)
ሰዓት፦ ከሌሊቱ 5.00 – ቀኑ 6.30 ሰዓት (23.00 fri – 12.30 Sat )
ቦታ፦ Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko (Läntinen Valkoisenlähteentie 48)

ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ
ቀን ፦ እሑድ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፳፻፰ (Sat Jan 3 2016)
ሰዓት፦ ሰዓት 9:30 – 19:20 (15:30 -19:20 )
ቦታ፦ Opastinsilta 6A, Helsinki

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!

በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
ፊንላንድ

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *