Monthly Archives: August 2016


29
Aug 2016
የጻድቁ አባታችን በዓለ ዕረፍት ተከብሮ ዋለ

በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖትን የበዓለ ዕረፍታቸውን ዓመታዊ ክብረ በዓል ነሐሴ 22 ቀን 2008ዓ.ም. (28.08.16 እ.ኤ.አ) ፣ ቮሳሪ በሚገኘው የፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሶፊያ ማዕከል በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ፡፡ በበዓሉ ላይ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱ ፈቃድ የደብሩ አስተዳዳሪ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ቀሲስ አንገሶም በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ እና የደብሩ ዲያቆናትና ቀሳውስት መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ከስዊድን) ፣ ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ(ከኢትዮጵያ)፣ መምህር ፍቃዱ ሣህሌ(ከኢትዮጵያ) ፣ እንዲሁም ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ሕጻናትና በፊንላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያና......

Read More


29
Aug 2016
"ኢትዮጵያ ዛሬ" በሚል መሪ ቃል  ዐውደ ጥናት ተካሄደ

ነሐሴ 21 2008 ዓ.ም. (27.08.16 እ.ኤ.አ) በሶፈያ የባህል ማዕከል ”ኢትዮጵያ ዛሬ (Etiopia tänään)” በሚል መሪ ቃል በሶፍያ የባህል ማዕከል እና በፊኒሽ ኦርቶዶክስ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት ተካሄደ። ዐውደ ጥናቱ የተለያዩ መርሀግብሮችን በማካተት ከቀኑ 12፡00 እስከ 18፡00 ቀጥሎ ውሏል። ከቀኑ 12-14 ሰዓት በዕለቱ በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጋባዥነት ከስዊድን የሉንድ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ታሪክ በሚመለከት ጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ ፣ በቦታው ለታደሙት የጉባኤው ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡ በማስከተልም። ወ/ሪት ፌቨን ትዕግሥቱ “ቱሪዝም በኢትዮጵያ” በተሰኘ ርዕስ የኢትዮጵያን ዋና ዋና......

Read More


26
Aug 2016
አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍት የዋዜማ በዓል በድምቀት ተከበረ!

በፊላንድ ሄልሲንኪ አሉንኩላን ቤተክርስቲያን የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍታቸውን አስመልክቶ የዋዜማ ጉባኤ የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ፤ ተጋባዥ እንግዶች መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ከስዊድን) ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ(ከኢትዮጵያ) መምህር ፍቃዱ ሣህሌ(ከኢትዮጵያ) ፣ የሰንበት ት/ቤቱ መዘምህራን እና ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ተከብሯል፡፡ ሕጻናትም በፕሮግራሙ ላይ ዝማሬን አቅርበዋል። በነገውም ዕለት ከቀኑ 12:00 ሰዓት እስከ 18:00 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 22:00 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የአዳር መንፈሳዊ አገልግሎቶች በሶፊያ የባህል አዳራሽ እንደሚቀጥልም ተገልጾዋል። በዋዜማ ሌሊቱን በማህሌት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በጋራ በመሆን መንፈሳዊ አገልግሎት ይቀጥላል።...

Read More


18
Aug 2016
በቫሳ ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዳሴና የሥርዐተ ጥምቀት አገልግሎት ተሰጠ

በቫሳና አካባቢው ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እሑድ ነሐሴ 8 2008 ዓ.ም. ከሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ወደ ስፍራው በተጓዙ አገልጋዮች አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዳሴና የሥርዓተ ጥምቀት አገልግሎት ተከናውኗል፡፡ በዕለቱ በተካሄደው  መንፈሳዊ አገልግሎት በአካባቢው የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች የተሳተፉ ሲሆን ለሰባት ሕጻናትም  ሥርዓተ ጥምቀት ተፈፅሟል፡፡ ቫሳ ውስጥ መንፈሳዊ አገልግሎት በመደበኛ የሰንበት ጉባኤ አማካኘነት ላለፉት አራት ዓመታት ይሰጥ እንደነበርና፣ የቅዳሴ አገልግሎት ለማግኘት ግን ሕዝበ ክርስቲያኑ ወደ ሄልሲንኪ በመጓዝ  ወይም በሁለት ወር አንድ ጊዜ  በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሚዘጋጅ መንፈሳዊ አገልግሎት ይሳተፍ እንደነበር በአገልግሎቱ ላይ የተገኙ ምእመን ገልጸዋል፡፡ በአግልግሎቱ ላይ የተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች......

Read More


05
Aug 2016
ጾመ ፍልሰታ

ጾመ ፍልሰታ ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጉም ስናነሣ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጣ /የተገኘ/ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ ከምድር ከመቃብር መለየት፣ ማረግ፤ ወደ ላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ያመለክታል፡፡ በዚህ መሠረት ጾመ ፍልሰታ በአጠቃላይ የእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋዋን ከመቃብር መለየትና ወደ ገነት ማረጉን የሚያመለክት ሲሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን ምዕመናን እንዲጾሙት ከምታዘው ሰባቱ አጽዋማት አንዱና ለዓመቱ ደግሞ የመጨረሻው ጾም ነው፡፡  ይህ ጾመ ፍልሰታ በሌላ አጠራር ጾመ ማርያምም በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ወቅት በብዛት የሚወሳው /የሚነገረው/ ቃለ እግዚአብሔር በአብዛኛው ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የተያያዘ በመሆኑና የእርስዋ የሥጋዋ ፍልሰት መታሰቢያ በመሆኑ ጾመ ማርያም ተባለ፡፡ ነገር ከስሩ ውኃ ከጥሩ እንዲሉ አበው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ይህንን የእመቤታችንን ጾም ለምን እንደምታከብር ለመዘርዘር እንወዳለን፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል......

Read More