Daily Archives: August 29, 2016


29
Aug 2016
የጻድቁ አባታችን በዓለ ዕረፍት ተከብሮ ዋለ

በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖትን የበዓለ ዕረፍታቸውን ዓመታዊ ክብረ በዓል ነሐሴ 22 ቀን 2008ዓ.ም. (28.08.16 እ.ኤ.አ) ፣ ቮሳሪ በሚገኘው የፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሶፊያ ማዕከል በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ፡፡ በበዓሉ ላይ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱ ፈቃድ የደብሩ አስተዳዳሪ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ቀሲስ አንገሶም በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ እና የደብሩ ዲያቆናትና ቀሳውስት መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ከስዊድን) ፣ ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ(ከኢትዮጵያ)፣ መምህር ፍቃዱ ሣህሌ(ከኢትዮጵያ) ፣ እንዲሁም ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ሕጻናትና በፊንላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያና......

Read More


29
Aug 2016
"ኢትዮጵያ ዛሬ" በሚል መሪ ቃል  ዐውደ ጥናት ተካሄደ

ነሐሴ 21 2008 ዓ.ም. (27.08.16 እ.ኤ.አ) በሶፈያ የባህል ማዕከል ”ኢትዮጵያ ዛሬ (Etiopia tänään)” በሚል መሪ ቃል በሶፍያ የባህል ማዕከል እና በፊኒሽ ኦርቶዶክስ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት ተካሄደ። ዐውደ ጥናቱ የተለያዩ መርሀግብሮችን በማካተት ከቀኑ 12፡00 እስከ 18፡00 ቀጥሎ ውሏል። ከቀኑ 12-14 ሰዓት በዕለቱ በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጋባዥነት ከስዊድን የሉንድ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ታሪክ በሚመለከት ጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ ፣ በቦታው ለታደሙት የጉባኤው ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡ በማስከተልም። ወ/ሪት ፌቨን ትዕግሥቱ “ቱሪዝም በኢትዮጵያ” በተሰኘ ርዕስ የኢትዮጵያን ዋና ዋና......

Read More