Monthly Archives: March 2016


28
Mar 2016
እናትና አባትህን አክብር (ለሕፃናት)

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች ደህና ናችሁ በዛሬው የመጀመሪያ ጽሑፋችን እናትና አባትን ስለማክበር እንማማራለን ስለዚህ በደንብ ተከታተሉን፡፡ ከነብየ እግዚአብሔር ሙሴ የኦሪት መጻህፍት መካከል አንዱ በሆነው በኦሪት ዘዳግም 5÷16 ላይ እናትና አባትን ስለማክበር እንድህ በማለት ተናተናግሯል ፡- “እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፣ መልካምም እንዲሆንልህ እናትና አባትህን አክብር፡፡” ዘዳግም 5÷16 ልጆች ከአሥርቱ ትዕዛዛት መካከል አንዱ እናትና አባትህን አክብር የሚለው ነው፡፡ እግዚአብሔር እናትና አባታችንን ካከበርን በምድር ላይ ስንኖር ዕድሜያችን ረዥም እንደሚሆንና፤ በዚህ ዕድሜያችንም መልካም የሆነ ነገር እንደሚያደርግልን ቃል ገብቶልናል፡፡ ለእናትና ለአባታችን ስንታዘዝ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚደሰትና እድሜያችንን እንደሚያረዝምልን ሁሉ ካልታዘዝን ደግሞ ያዝንብናል፡፡ እናትና አባቱን የማያከብር፣ ስድብ......

Read More


28
Mar 2016
እኛንም ያድነናል (ለሕፃናት)

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች ? ደህና ናችሁ? እረፍት እንዴት ነው? የዚህ በሁለት ወር ክረምት እረፍታችሁን እንዴት እያሳለፋችሁ ነው? ልጆች ቤተሰባችሁን በመላላክ ሥራ በማገዝ እያገለገላችሁ ነው? በተለይ ደግሞ በቤተክርስቲያን ተገኝታችሁ ትምህርት ቃለ እግዚአብሄርን በመማር በዝማሬ እግዚአብሄርን እያመሰገናችሁ ነው? እንደዚህ ከሆነ በርቱ እሺ እግዚአብሔር የሚወደው እንደዚህ አይነቱን ነው፡፡ እሺ ልጆች ዛሬ ያቀረብንላችሁ ሐምሌ 19 የሚከበረውን ቅዱስ ገብርኤል ስላዳናቸው አንድ እናትና አንድ ልጅ ታሪክ አዘጋጅተንላችኋል በትዕግስት ተከታተሉን እሺ፡፡ የሕፃኑ ስም ቅዱስ ቂርቆስ ሲሆን የእናቱ ስም ደግሞ ቅድስት ኢየሉጣ ትባላለች አባቱ ቆዝሞስ ይባላል፡፡ ሐገሩ ሮም አንጌቤ ነው፡፡ ዲዮቅልጥያኖስ የተባለ ንጉሥ በነገሠበት ጊዜ በ303 ዓ.ም. አብያተ ክርስቲያናትን ማፈራረስ......

Read More


27
Mar 2016
ዓሣ አጥማጁ ስምዖን(ለሕፃናት)

በአንድ ወቅት ምን ሆነ መሰላችሁ ጌታችን በባህር ዳር ቆሞ ሕዝብን ያስተምር ነበር ሕዝቡም ጌታችን የሚያስተምረውን ትምህርት በደንብ ይከታተሉት ነበር፡፡ ጌታችንም ድምጹ ለብዙ ሰዎች እንዲሰማ ወደ ስምዖን ታንኳ ላይ ወጣ፡፡ በታንኳይቱም ውስጥ ተቀምጦ ሕዝቡን አስተማራቸው፡፡ ትምህርቱንም ሲጨርስ ሁሉም ሰው ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ ሲማሩ ከነበሩት መካከል አንዱ ስምዖን ነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ ሌሊቱን ሁሉ ምንም ዓሣ ስላላጠመደ ተጨንቆ ነበር፡፡ ለምን መሰላችሁ ልጆች የስምዖን ቤተሰቦች ስምዖን የሚያመጣውን ዓሣ ይጠባበቁ ስለነበረ ነው፡፡ ስምዖን ዓሣ ሳይዝ ወደ ቤቱ ከገባ ቤተሰብ ሁሉ ሳይበላ ነው የሚያድረው ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ልጆች እግዚአብሔር የስምዖን ቤተ ሰቦች ተርበው እንዲያድሩ አላደረጋቸውም፡፡ ሌላው ደግሞ......

Read More


26
Mar 2016
አትዋሹ (ለሕፃናት)

በድሮ ጊዜ ክርስቲያኖች በአንድነት ይኖሩ ነበር፡፡ በመካከላቸውም የሁሉ ገንዘብ በአንድነት ነበር አንጂ “ይህ የእኔ ገንዘብ ነው” የሚል አልነበረም ከእነርሱም አንድም ችግረኛ አልነበረም፤ ቤትና መሬት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ ገንዘቡን ያመጡ ነበር፡፡ አምጥተውም በሐዋርያት እግር ስር ያስቀምጡ ነበር፡፡ ሐዋርያትም ለእያንዳንዱ እንደፍላጎቱ ይሰጡ ነበር፡፡ ሐዋርያት ስሙን ዮሴፍ እያሉ የሚጠሩት በርናባስ የተባለ ሰው ነበር፡፡ የእርሻ መሬትም ነበረው፡፡መሬቱንም ሸጦ ገንዘቡን በሐዋርያት እግር ስር አስቀመጠው ከሐዋርያትም ማኅበር ተቀላቀለ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ልጆች ሐናንያና ሰጲራ የተባሉ ባልና ሚስቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ ባልና ሚስቶች መሬታቸውን ሸጡ፡፡ እርስ በርሳቸውም ተማከሩና ከሸጡት ዋጋ ግማሹን ለራሳቸው ወሰዱና የሸጥነው በዚህ ዋጋ ነው ብለው ግማሹን በሐዋርያት......

Read More