Monthly Archives: January 2016


01
Jan 2016
የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን የልደታቸው ንግሥ በዓል የፊታችን ቅዳሜ  ይከበራል

+ + + በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። “አእምሩ ከመ ተሰብሐ እግዚአብሔር በጻድቁ” .መዝ. 4,3 “እግዚአብሔር በጻድቁ እንደተመሰገነ እወቁ ” መዝ .4፣ 3 የተከበራችሁ ምእመናንና ምእመናት! እግዚአብሔር ቢፈቅድ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን የልደታቸው ንግሥ በዓል የፊታችን ቅዳሜ ታኅሣሥ ፳፫ (Sat Jan 2) በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ይከበራል ። በዕለቱም የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡነ እንጦንስ፣ እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ካህናት እና ዲያቆናት ይገኛሉ።ሥርዓተ ዋዜማው ከምሽት ፭ (23:00) ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል። የሌሊቱም ሥርዓተ ማኃሌት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ምእመናን እና ምእመናት በሚገኙበት ተቁሞ ይታደራል። ሥርዓተ ቅዳሴው በሊቀ ጳጳሱ......

Read More