Monthly Archives: January 2018


31
Jan 2018

መልካም ጓደኛ.pdf መልካም ጓደኛ  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን በዚህ በምንኖርበት አለም ይብዛም ይነስም አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጓደኛ ይኖረናል። በእርግጥ በዚህ ጽሁፍ ዉስጥ ለመግለጽ የተፈለገዉ የወንድ ወይም የሴትን የተቃራኒ ፆታ የፍቅር ጓደኝነትን ሳይሆን መልካም የልብ ጓደኛ ማለት ምን ማለት ነዉ? የሚለዉን ለማየት ሲሆን ምናልባትም ብዙዎቻችን በተለምዶ እገሌ እኮ የእገሌ የልብ ጓደኛዉ ነዉ፤ እገሊትም ለእገሊት የልብ ጓደኛዋ ናት ስንልም እንሰማለን። በአንጻሩ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች እገሌ ወይም እገሊት እኮ ጓደኛ አይወጣለትም ወይም አይወጣላትም እንዲያዉ ምክንያቱ ምን ይሆን? በማለት አስተያየት እንሰጣለን። ይሁን እንጅ የልብ ጓደኛ ብለን ስንናገር መለኪያችን ከምን አንጻር እንደሆነ......

Read More


16
Jan 2018
የ2018 ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰሜን ምዕራብ አውሮፖ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የአጥቢያው ምእመናን በተገኙበት እሑድ ጥር 6 2010ዓ.ም. ወይም Jan 14.2018 በፑኪንማኪ የመሰባሰቢያ አዳራሽ እ.ኤ.አ. የ2018 ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ፡፡ በጉባኤው መጀመሪያ ላይ የ2017 የክፍሎች የዕቅድ አፈጻጸም እና፣  የሒሳብ ሪፖርት እንዲሁም  የኦዲት ምርመራ ሪፖርቶች ለጉባኤው ቀርበዋል፡፡  ሪፖርቶቹ ከቀረቡ በኋላ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ለቀረቡ ጥያቄዎችም ከክፍል ተወካዮች እና ከደብሩ አስተዳዳሪ ምላሽ ተሰጥቶ ጉባኤው ሪፖርቶቹን አጽድቋል፡፡ በመቀጠልም እ.ኤ.አ. የ2018 በጀት ዓመት የክፍሎች ዕቅድ ለጉባኤው የቀረበ ሲሆን የቀረበውን ዕቅድ ተከትሎም ከተሳታፊዎች አስተያየት እና ማሳሰቢያ የተሰጠ ሲሆን በተለይ......

Read More


01
Jan 2018
የአቡነ ተክለሃይማኖት የልደት በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ

በየዓመቱ ታኅሣሥ 24 ቀን የሚከበረው የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 21 ቀን 2010ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በትላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ ከኢትዮጵያ በመጡ መምህር ዲ.ዶ.ር ቴዎድሮስ በለጠ ከዋዜማው ምሽት ጀምሮ ሥርዓተ ማኅሌቱ እስኪጀመር ድረስ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን፣ የስካንድኖብያ ቤተክህነት ሊቀ ካህናትና በዴንማርክ የኮፐን ሀገን ደብረ ምሕረት አማኑኤል እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አቢያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ዘሚካኤል ፣ በፊንላንድ ሄልሲንኪ የደብረ ሰላም መድኀኔዓለም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ምእምራን ቀሲስ ዮሴፍ ፣ ካህናትና ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ ሕጻናት ፣ ከሄልሲንኪና እና......

Read More