Monthly Archives: June 2017


20
Jun 2017
የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊው በዓል በቱርኩ -ፊላንድ በድምቀት ተከበረ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ  በየዓመቱ ሰኔ 12 ቀን  የሚከበረው   ዓመታዊው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ  በዓል በቱርኩ- ፊላንድ  ሰኔ 10/2009 ዓ .ም በደመቀ ሁኔታ  ተከበረ። በዘንድሮ ዓመት  ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ በርካታ ምእመናን ወደ ቱርኩ ተጉዘው በዓሉን ያከበሩ ሲሆን ፣ ከመቼውም ጊዜ  በበለጠ መልኩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሐዶ  እና የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አቢያተ ክርስቲያናት  ካህናት እና ምእመናን በጋራ በተገኙበት በማኅሌትና  በቅዳሴ ከማለዳው  የተጀመረው ክብረ በዓል ቀኑን ሙሉ ቀጥሎ  ከቅዳሴው ፍፃሜ በኋላም  ትምህርትና  እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ  ዝግጅቶች ቀርበዋል ። በፊላንድ  ሄልሲንኪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን የደብረ አሚን አቡነ  ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን    አስተዳዳሪ  መጋቤ ብሉይ ቀሲስ......

Read More


13
Jun 2017
የተመራቂ ተማሪዎች ልዩ መርሃግብር ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰኔ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም (June 11, 2017) ዓ.ም በቀለም ትምህርታቸው ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለተመረቁ ተማሪዎች ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጀ። በመርሃ ግብሩ መጀመሪያ በደብሩ የስብከተ ወንጌል ክፍል ተጠሪ በተላለፈው መልእክት በዘንድሮ ዓመት የተጀመረው ይህ የተመራቂዎች መርሃ ግብር ወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን መንፈሳዊውንም ትምህርት በሰንበት ትምህርት ቤት ተመዝግበው ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ከዛሬ በኋላ ተመራቂዎቹ በእውቀታቸውና በመሳሰለው ሁሉ ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ ቀርቧል ። መርሃ......

Read More