Monthly Archives: September 2017


29
Sep 2017
የመስቀል ደመራ በዓል ለሁለተኛ ጊዜ በሄልሲንኪ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪደብረ አሚን አቡነተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በሄልሲንኪ ከተማ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል ለሁለተኛ ጊዜ ተከበረ። ከባለፈው ዓመት በተለየ መልኩ የደመራ አዘጋጅ ኮሚቴ ተመርጦ ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎ መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ከ 17፡30 – 20፡30 በተካሄደው የደመራ ሥነ ሥርዓት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፊንላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ምእመናን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የልዩ ልዩ ቤተ እምነት መሪዎች ፡ የመንግሥት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሓላፊዎችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በበዓሉ ተገኝተዋል፡፡ በደብሩ ካህናትና ዲያቆናት መሪነት ዕለቱን የሚያዘክር ስብሐተ እግዚአብሔር ከደረሰ  በኋላም በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዓሉን የሚመለከት ወረብ ቀርቧል፡፡......

Read More


05
Sep 2017
የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ የእረፍት  ክብረ በዓል  በታላቅ ድምቀት ተከበረ ።  

ከነሐሴ 24 ቀን እስከ 28 ፥ 2009 ዓ.ም.  ድረስ በታላቅና በልዩ ድምቀት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሲከበር በሰነበተው በዚህ ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ግብዣ የተደረገላቸው በአውሮፓ ከሚገኙ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች መካከል በኖርዌይ ስታቫንገ  የደብረ ገነት መድኃኔዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የስካንዴኔቭያን ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ፀሐፊ መጋቤ ምሥጢር አባ ቴዎድሮስ አካሉ፣ በኦስትሪያ ቬና የደብረ ሲና  ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉያት ቆሞስ አባ ዘተክለሃይማኖት፣ በኖርዌ ኦስሎ የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቀሲስ ተስፋ ሚካኤል  እንዲሁም በፊንላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያ......

Read More