Monthly Archives: November 2017


24
Nov 2017
ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ኅዳር ፲፭

ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡......

Read More


23
Nov 2017
የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ሕዳር 12 ቀን የሚከበረው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ከትላንት በስትያ ከሄልሲንኪ ከተማ ተጉዘው በቦታው በተገኙ ኢትዮጵያውናን እና ኤርትራውናን ሕዳር 9 ቀን 2010 ዓ.ም በፊላንድ በድምቀት  ተክብሯል። ከፊላንድ ዋና ከተማ ሄልሲንኪ 150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በቱርኩ ከተማ በሰማዕቱ በቅዱስ አሌክሳንደር የፊላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከማላዳው  ጀምሮ በቅዳሴ  የተጀመረው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ቀኑን ሙሉ የተለያዩ መንፈሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች ቀርበውበታል ። በፊላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ የወንጌል ትምህርት ሰጥተዋል።የደብረ አሚን አቡነ......

Read More