Daily Archives: September 29, 2017


29
Sep 2017
የመስቀል ደመራ በዓል ለሁለተኛ ጊዜ በሄልሲንኪ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪደብረ አሚን አቡነተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በሄልሲንኪ ከተማ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል ለሁለተኛ ጊዜ ተከበረ። ከባለፈው ዓመት በተለየ መልኩ የደመራ አዘጋጅ ኮሚቴ ተመርጦ ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎ መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ከ 17፡30 – 20፡30 በተካሄደው የደመራ ሥነ ሥርዓት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፊንላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ምእመናን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የልዩ ልዩ ቤተ እምነት መሪዎች ፡ የመንግሥት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሓላፊዎችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በበዓሉ ተገኝተዋል፡፡ በደብሩ ካህናትና ዲያቆናት መሪነት ዕለቱን የሚያዘክር ስብሐተ እግዚአብሔር ከደረሰ  በኋላም በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዓሉን የሚመለከት ወረብ ቀርቧል፡፡......

Read More