Monthly Archives: April 2017


13
Apr 2017
የሆሣዕና በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሚያዚያ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. የሆሣዕና በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። በዕለቱም በየዓመቱ እንደሚከናወነው ሁሉ ቅዳሴ ሥርዓቱ በተለየ ሁኔታ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት ከተከናወነ በኋላ በቀሲስ ዶክተር አምሳሉ ተፈራ ስለ ሆሣዕና በዓል አጠር ያለ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ የሆሣዕና በዓል ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አዕሩግም ሕፃናትም ‹‹ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፣ሆሣዕና በአርያም›› እያሉ ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል መሆኑን፤ ‹ሆሣዕና› የሚለው ቃል ‹ሆሼዕናህ› ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተወሰደ ሲሆን ፣......

Read More


13
Apr 2017
በሶፊያ ባህል ማዕከል ልዩ ዐውደ ጥናት ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እና በፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሶፊያ ባህል ማዕከል ትብብር ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. በሶፊያ የባህል ማዕከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትን እና የቅዱስ ያሬድን ዜማ በሚመለከት ልዩ ዐውደ ጥናት ተካሄደ፡፡ በዐውደ ጥናቱም ላይ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፈቃድ፣ የአጥቢያው ምእመናን፣ የፊንሽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች እና የሀገሪቱ ዜጎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በመጀመሪያ ገዳማዊ ሕይወት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሚል ርዕስ የገዳማዊ ሕይወት አጀማመር፣ ያበረከተው አስተዋጽዖ እና......

Read More