Monthly Archives: January 2017


25
Jan 2017
በዓለ ጥምቀት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጥር 13 ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ቲኩሪላ በሚገኘው በፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። በዕለቱ በተያዘው መርሃ ግብር መሠረት ሥርዓተ ቅዳሴው ከተከናወነ በኋላ የባህረ ጥምቀቱ ሥርዓተ ጸሎት ተደርሶ ህዝቡም ጸበል ተረጭቶ የበረከቱ ተካፋይ ሆኗል፡፡በመቀጠልም በደብሩ መዘምራን ዕለቱን የተመለከተ  ያሬዳዊ ዜማ የቀረበ ሲሆን  በመጨረሻም በደብሩ አስተዳዳሪ በመጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ   ትምህርተ  ወንጌል  እና ጸሎተ ቡራኬ ከተሰጠ በኋላ  የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።...

Read More


22
Jan 2017
የልደትን በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የሕጻናት መርሐ ግብር ተካሄደ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል የሕፃናትና  አዳጊ ንዑስ ክፍል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ እሑድ ታኅሣሥ 30 ቀን 2009 ዓ.ም (January 8, 2017) ከሰዓት በኋላ ልዩ የሕጻናት እና የአዳጊ ልጆች መርሐ ግብር ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ መጀመሪያ ላይ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ በተላለፈው መልእክት ሕፃናትና  አዳጊ ልጆች የነገ የቤተ ክርስቲያናችን ተረካቢዎች በመሆናቸው  ትኩረት፣ ፍቅርንና ጊዜን ሰጥተን መሥራት የሚጠበቅብን መሆኑን እና ጥሩ ምሳሌ መሆን ከሁሉም ምእመናን የሚጠበቅ መሆኑ ተገልጿል። ይህን መሰል ልዩ መርሐ ግብር ለልጆች......

Read More


07
Jan 2017
ልደተ ክርስቶስ /የገና በዓል/ - ለሕጻናት

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደህና ናችሁ? ዛሬ ስለጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት /ገና በዓል/ እንነግራችኋለን፡፡ በደንብ ተከታተሉን፡፡ እሺ? ልጆች በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ፡፡ አውግስጦስ ቄሳር የተባለ ንጉሥ ሰው ሁሉ ይቆጠር ዘንድ አዘዘ፡፡ በትእዛዙ መሠረትም ሰው ሁሉ ሊቆጠር ወደየትውልድ ከተማው ሄደ፡፡ ዮሴፍና እመቤታችንም ሊቆጠሩ ከናዝሬት ወደ ትውልድ ሥፍራቸው ወደ ቤተልሔም ሄዱ፡፡ በቤተልሔም ሳሉም እመቤታችን የምትወልድበት ቀን ደረሰ፡፡ በዚያ ሥፍራም ብዙ እንግዳ ስለነበር እነ ዮሴፍ የሚያርፉበት ቦታ አላገኙም ነበር፡፡ ማደርያም ስላልነበራቸው በከብቶች ማደርያ በበረት ውስጥ እመቤታችን ልጅዋን ወለደችው፡፡ በጨርቅ ጠቅልላ እዛው በበረት ውስጥ አስተኛችው፤ በዚያ ሀገር ይኖሩ የነበሩ እረኞችም ሌሊት ከብቶቻቸውን ይጠብቁ ነበር፤......

Read More


07
Jan 2017
ልደተ ክርስቶስ (ገና)

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ!!! ከጌታችን ከልደቱ ያገኘነው ምንድን ነው? ዳግም ልደት በአዳም በደል ምክንያት አጥተነው የነበረው ልጅነታችንን ክርስቶስ በልደቱ ዳግመኛ እንደመለሰልን ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 1፥12 በማለት ገልጾታል። ሰላም በጌታችን ልደት ለዓለም ሁሉ የሚሆን ዘላለማዊ ሰላም ተገኝቷል። ይህም “ክብር እግዚአብሔር በሰማያት ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጐ ፈቃድ” እያሉ ቅዱሳን መላእክት በመዘመራቸው ተረጋግጧል። ሉቃ 2፥14። ስለዚህ በክርስቶስ ያገኘነው እውነተኛ ሰላም በእኛ ጸንቶ እንዲኖር ዘወትር በጾምና በጸሎት እየተጋን ስለሰላም የምንማፀን ሆነን ልንገኝ ይገባል። ሰላም የክርስትና መታወቂያ አርማ......

Read More


03
Jan 2017
የ2009 ዓ.ም. የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ልደት ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት  ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 24 ቀን የሚውለውን የጻድቁ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ቲኩሪላ በሚገኘው የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን  ተከበረ። በዓሉ ታኅሣሥ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ፣  የደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ ሕጻናት፣ ከሄልሲንኪና እና ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ምእመናን እና ምእመናት እንዲሁም በፊንላንድ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኤርትራ ኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት ተከብሯል። በዓሉ ዓርብ ምሽት በጸሎት ከተጀመረ በኋላ የአቡነ ተክለ......

Read More