Daily Archives: April 30, 2016


30
Apr 2016
ቀዳሚት ሥዑር

በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አድሮ የዋለባት ዕለት በመሆኗ «ቀዳሚት ሥዑር » ትሰኛለች፡፡ ቀዳሚት ሥዑር የተባለችው በዓመት አንድ ቀን ስለ ሚጾምባት ነው፡፡ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያም ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንስተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ። አልቀመሱም ፡፡ አምላካቸው በመቃብር ስላደረ ዕለቷን ሞቱን በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም ውለዋል። ከቅዱሳን ሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን በመጾምና በመጸለይ ዕለቷ እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆች የተቻላቸው ከዓርብ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ ቀምሰው ቅዳሜን በመጾም/ በማክፈል ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ ለምን......

Read More


30
Apr 2016
የስቅለት በዓል ዛሬ በደብራችን በድምቀት ተከብሮ ዋለ

የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል ዛሬ በደብራችን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ በዕለቱንም ከጠዋት ጀምሮ በርካታ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ጌታችን ስለኛ ብሎ የተቀበለውን መከራና ስቃይ እያሰቡ በመጸለይና በመስገድ አሳልፈዋል፡፡ በደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የ5500 ዓመት የዕዳ ደብዳቤያችን የተደመሰሰበት የተወገደበት ፣ የሰው ልጅ የኃጢአት ቀንበር የተሰበረበት፣ የሞትና የጨለማ መጋረጃ የተቀደደበት፣ ፍፁም ፍቅር የተገለጠበት ዕለት መሆኑን አስተምረዋል፡፡ እኛም በየትኛውም ዓለም የምንኖር ምእመናን ከሁሉም በላይ የሚበልጠው ፍቅር ነውና ፍቅርን ገንዘብ እናድርግ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በማያያዝም ነገ ትንሣአኤ......

Read More