Daily Archives: April 22, 2016


22
Apr 2016
በሄልሲንኪ ከተማ አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም አንተው” በሚል መሪ ቃል ልዩ የአውደ ርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያካሄድ አስታወቀ። ግንቦት 12 2008 ዓም በሄልሲንኪ ከተማ ይካሄዳል የተባለው መርሐ ግብር አላማው  የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና እንዲኖረው ማድረግ። ወደፊት ስለ ተረካቢ ህፃናትና ከፊንላንድ መንግስትና ለሚመለከታቸው ግንዛቤ መፍጠር በፊንላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመሰራረት ታሪክና ዛሬ ያለንበትን ደረጃ ማስተዋወቅ ናቸው። በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ ቤተ እምነቶች ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንግዶች ይጋበዛሉ።አውደ ርዕዩ ከቤተ ክርስቲያኗ 5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ጋር በጋራ ይከበራል።...

Read More