07
Apr 2016
ሰማዕት ‹‹ሰምዐ›› ከሚል የግእዝ ቃል የተወሰደ ሲሆን፤ ትርጉሙም ያየነውን፣ የሰማነውን መመስክር መቻል እንደሆነ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ስዋስወ ወግስ መዝገበ ቃላት ገጽ 671 ይነግረናል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹እኔ ለእውነት ለመመስከር መጥቻለሁ›› በማለት እውነትን እንድንመሰክር አብነት ሆኖናል /ዮሐ.18፥37/፡፡ ሰማዕትነት በሃይማኖታዊ ትርጉሙ ስንመለከተው ስለ እግዚአብሔር፣ ስለቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ስለ ሃይማኖታቸው በእውነት በመመስከራቸው ጀርባቸውን ለግርፋት፣ ሰውነታቸውን ለእሳት፣ እግራቸውን ለሰንሰለት፣ አንገታቸውን ለስለት አሳልፈው ለሰጡ፤ በድንጊያ ተወግረው በመንኮራኩር ተፈጭተው በጦር ተወግተው አልያም በግዞትና በስደት በዱር በገደል ተንከራተው ለዐረፉ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳት እናቶች የሚሰጥና ተጋድሎአቸውን ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊው እመቤታችንን ባመሰገነበት ድርሳኑ “ሰማዕታት የዚህችን......
Read More