Start Blog Type 1 (Full Width Image) and Sidbar

07
Apr 2016
ነትገ ማይ አይኅ

”ወበጽርሑሰ ኵሉ ይብል ስብሐት እግዚአብሔር ያስተጋብኦ ለማየ አይኅ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል እግዚአብሔር የጥፋት ውሃን ሰብስቧልና” መዝ ፳፰፥፱ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በዚህ መዝሙሩ ላይ፦ ምዕመናን ለአምላካቸው የአምልኮ መገለጫ የሆኑትን ምስጋናና ስግደት ሊያደርጉ እንደሚገባቸው በመጀመሪያዎቹ ስንኞች ላይ አስፍሯል፦ ”በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ” – እንዲል። በሚቀጥሉት ስንኞች ደግሞ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ አምላክ እንደሆነ ሰብኳል። ”የክብር አምላክ አንጐደጐደ” በማለት በብዙ ምሳሌ አስተምሯል፤ የሊባኖስ ዝግባን፣ ውሃን፣ እሳትን፣ የቃዴስን ምድረ በዳ እየጠቀሰ ተናግሯል። ይህ ሁሉ የእስራኤላውያን የአምልኮ ታሪክና የእግዚአብሔርን ተአምራት የሚያስታውስ ነው፤ ይህውም በምድረ በዳ እና በመሳፍንት ዘመን ሁሉ የነበረው ነው፦ ውሃውን ያለ ግድብ ሲያቆም፣ ከጭንጫ ሲያፈልቅ፣......

Read More


07
Apr 2016
ጸሎት ክፍል 2

በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ “አንትሙሰ ሶበት ጸልዩ ስመ ዝበሉ፡፡” ማቴ.6፥ እናንተስ በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ በላችሁ ጸልዩ “አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁ በምድር ይሁን…. በዚህ የጸሎት ክፍል ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ81 መጻሕፍት የተገኙ አምስት ቁም ነገሮችን አስተምሯል፡፡ ሃይማኖት ተስፋ ፍቅር ትሕትና ጸሎት 1.   ሃይማኖት፡- ሃይማኖት ማለት በዐይናችን ያላየነውን አምላክ አባታችን ሆይ ሲሉ መኖር ነው ቀደም ሲል የነበሩ አበው ነቢያት ሲጸልዩ እግዚእነ አምላክነ ንጉሥነ እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ ይህም ከግብርናተ ዲያብሎስ /ለዲያብሎስ ከመገዛት/ እንዳልዳኑ ለማጠየቅ ነው፡፡ እኛን ግን ከግብርናተ ዲያብሎስ ነጻ አውጥቻችኋለሁ ሲል አባታችን ሆይ......

Read More


07
Apr 2016
ጸሎት ክፍል 1

በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ጸሎት ጸለየ፡- ለመነ፣ ጠየቀ አማለደ፣ ማለደ ካለው የግዕዝ ቃል የወጣ ቃል ነው፡፡ ጸሎት ማለት ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እግዚአብሔርን ማመስገን መለመን፣ መጠየቅ፣ መማለድ፣ መማፀን ነው፡፡ “ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር፡፡” አባታችን አዳምም ከመላእክት ተምሮ በየሰዓቱ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ ዲያብሎስ በእባብ አድሮ ወደ አዳም በመጣ ጊዜ ጸሎት እያደረገ ስለነበር ዲያብሎስን ድል ነሥቶታል ሔዋንን ግን ሥራ ፈትታ እግሯን ዘርግታ ስለአገኛት ድል ነስቷታል፡፡ ጸሎት ሰማእታት ከነደደ እሳት፣ ከተሳለ ስለት፣ ከአላውያን መኳንንት፣ ከአሕዛብ ነገሥታት ከዲያብሎስ ተንኮል እና ሽንገላ ዲያብሎስ በእነርሱ ላይ ከአጠመደው አሽከላ የዳኑበት ጋሻ ነው፡፡ ኤፌ.6፥10 21 ጸሎት፣ ሰው......

Read More


07
Apr 2016

በዲ/ን ኅብረት የሺጥላ ኪዳን የሚለው ቃል ‹‹ቃል›› ከሚለው ጋር እየተዛረፈ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲሰ ኪዳን ደግሞ ከ32 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ ‹‹ኪዳን›› ቃሉ ‹‹ተካየደ›› ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ምሕረት›› የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡ ‹‹ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አድርጋለሁ›› ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደፊትም ያደርጋል፡፡ (መዝ88.3) ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል......

Read More


Social Icons

Calendar

May 2024
M T W T F S S
 12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
2728293031  

instagram

    flickr

    instagram