Blog


11
Mar 2023

በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የቅዱስ ዑራኤል ጽዋዕ ማኅበር ተመሠረተ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እየተገለገሉ የሚገኙ በዩቫስኲላ ከተማ የሚኖሩ ምእመናን መጋቢት ፪/፳፻፲፭ ዓ.ም በቅዱስ ዑራኤል ስም የጽዋዕ ማኅበር መሠረቱ። በዝርወቱ ዓለም የሚኖሩ ምእመናን በየወሩ እየተሰበሰቡ በጋራ በአንድነት በቅዱሳን ስም የጽዋዕ ማኅበር መሥርተው ይጸልያሉ ፣ይማጸናሉ አመቺ በሆነ ጊዜም ቅዳሴ ይቀደስላቸዋል ፣ በዚሁ መሠረት በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የሚገኙ ምእመናን እጣ በመጣል በተደጋጋሚ ቅዱስ ዑራኤል በመውጣቱ በመልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ስም የጽዋዕ ማኅበር ተመሥርቷል ። በዕለቱ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ......

Read More


02
Feb 2023

ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም፥ በስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለጽጌ ሃይማኖት ስንበት ትምህርት ቤት ተተኪ መዘምራን ‹‹ ብላቴናነትን የመቀደስ ጥበብ በቤተ ክርስቲያን ›› በሚል ርእስ በመምህር ታደሰ ወርቁ ሥልጠና ተስጥቷል። ሥልጠናውን የወሰዶት አብዛኛዎቹ ብላቴናዎች በፊንላንድ ተወልደው የአደጉ ናቸው ። በዚህም የሥልጠና ርእሰ ጉዳይ የብላቴናነትና ብላቴናነትን የመቀደስ ምንነት፣ ብላቴናነትን የመቀደስ ጥበብ ምን ምን እንደሆነ ተዳስሷል። የደብሩም ተተኪ መዘምራን ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አንስተው፤ ለተነሱት ጥያቄዎች በአሥልጣኙና በደብሩ አስተዳዳሪ ሰፊ ማብራሪያይና መልስ ተስጥቷል።...

Read More


27
Jan 2023

On January 24, 2023, in the Diocese of Sweden, Scandinavia and Greek countries, in Helsinki, Finland, Debre Amin Abune Teklehaymont Church, a mandate was held that took into account the cognitive challenge faced by our Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. In the training program under the title of “The Sustainability of Spiritual Servants in Times of Crisis”, the General Manager of the Diocese of Sweden, Scandinavia and Greek Countries and the Administrator of Debre Amin Abune Teklehaymont Church of Helsinki, Finland; d.n. Tadesse Worku has given physical and online training to parish council......

Read More


25
Jan 2023

ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም፥ በስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ውቅታዊ ፈተና ታሳቢ ያደረገ ሥልጣን ተካሂዷል። በሥልጠናው መርሐ ግብር ‹‹ የመንፊሳዊ አገልጋዮች ሡታፌ በዘመነ ቀውስ ›› በሚል ርእስ÷በስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሰብሳቢነት፤ በመምህር ታደሰ ወርቁ ለሰበካ ጉባኤ አባላት፣ ለልዩ ልዩ ክፍል ሐላፊዎችና ለንዑስ ክፍል ተጠሪዎች በአካልና በበየነ መረብ ሥልጠና ተሰጥቷል። በዚህም ሥልጠና የመንፈሳዊ አገልጋዮች ለአገልግሎት የመታጨት ሂደቶች፣ በአሁን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የገጠማት......

Read More


22
Jan 2023

የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን፣ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሰሱ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኘበት በድምቀት ተከብሯል። የበዓሉ ሥነ ሥርዓት የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሆኑት በመልአከ አሚን የተመራ ሲሆን፤ በዓሉን የተመለከ ትምህርት ከኢትዮጵያ በመጡት በዲያቆን ታደሰ ወርቁ ትምህርት ተሰጥቷል። በፊንላንድ ተወልደው ያደጉ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት የጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ተተኪ መዘምራንም በዓሉን የሚያዘክረውን ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል።...

Read More


01
Nov 2022

በመ/ር አቤል አሰፋ (ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ) በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅብዓ ሜሮን የማፍላት የጸሎት መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። ቀድሞ ከግብፅ ተዘጋጅቶ ይመጣ የነበረው ቅብዓ ሜሮን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲዘጋጅ ይህ ለ፫ ተኛ ጊዜ ነው። ማለዳ ጠዋት ፲ ሰዓት በተጀመረው ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ; ምእመናንና ካህናት ለ፯ ተከታታይ ቀናት በጸሎት እንዲተባበሩ ቀደም ብሎ በቅዱስነታቸው ጥሪ ቀርቧል። ይህንኑ አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ......

Read More


29
Sep 2022
የ፳፻፲፭ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በሄልሲንኪ ፊንላንድ በደማቅ ሥነሥርዓት ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ማርያም አቢያተ ክርስቲያን በአንድነት የመስቀልን ደመራ በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት አከበሩ። በዕለቱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ካህናት እና ምእመናን ከመላዋ ፊንላንድ የመጡ በአንድነት በቦታው ተገኝተዋል።በተጨማሪም በክብር እንግድነትም የሂልሲንኪ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሊዮ ዋና ፀሐፊ ቀሲስ ላዛርዩስ ተገኝተው ለሕዝበ ክርስቲያኑ መልእክት አስተላልፈዋል።   በመጨረሻም የሁለቱ አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድና ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ አንገሶም ዕቁባይ ትምህርት ከሰጡ በኋላ ደመራው ተለኩሶ ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ዝማሬ ዘምረው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖአል።...

Read More


21
Aug 2022
የደብረ ታቦር በዓል በሄልሲንኪ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ

በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የደብረ ታቦር በዓል የደብሩ ሕጻናት አዳጊ ልጆች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል ። የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይሜኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት በተለይ በዝርወቱ ዓለም ተወልደው የሚያድጉ ተተኪው ትውልድ የበዓላትን አከባበር እንዲሁም ትውፊታዊውንም ቅብብል በተግባር ያውቁ ዘንድ እንዲያስችል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። ወላጆችም ለዚሁ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብለዋል ። በቀጣይ የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመትም እንዲሁ በደሜቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከበር ጠቁመዋል። በተያያዘ ዜና ነሐሴ 14 /2014 ዓ.ም በታምፔሬ ከተማ በታምፔሬ የሚገኙ የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጽዋዕ ማኅበር አባላት......

Read More


25
Jul 2021
የአገልግሎት ምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ

በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለወ/ሮ አለማች ገብረ ሚካኤል የአገልግሎት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጠ። በሀገረ ፊንላንድ ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ በመንፈሳዊ አገልግሎት በማኅበራዊ አገልግሎት ለሚታውቁት ወ/ሮ አለማች ፣ ሐምሌ ፲፯/፳፻፲፫ ዓ.ም በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት የምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ ። በዕለቱም በመርሐግብሩ የታደሙት ምእመናን ወ/ሮ አለማች በሀገረ ፊንላንድ በስደት ለሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ያዘነውን በማጽናናት ፣ በመጠየቅ የሀገረ ፊንላንድንም ሥርዓተ ሀገሩንም በማለማመድ ከፍተኛ አገልግሎት ማበርከታቸውን ተናግረዋል ። ወ/ሮ አለማች በተለይ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከታላቁ ካህን አባታቸውና ከለጋሷ እናታቸው የወረሱትን በጎ ተግባር ስደቱ ተጽእኖ ሳይፈጥርባቸው ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን......

Read More


26
Dec 2020

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንድኔቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ቤተክርስቲያን እሑድ ታኅሣሥ 11 ቀን /2013 (20.12.2020) በርቀት በስካይፔ ባካሄደው ዓመታዊ የአጥቢያ ምእመናን መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፈረንጆቹ ከ2021 ዓ.ም ጀምሮ በደብሩ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ቤተክርስቲያኗን የሚያገለግሉ አዲስ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላ ምርጫን አካሄዷል። ጠቅላላ ጉባኤውን በጸሎት ክፍተው የመሩት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ የዕለቱን አጀንዳዎች ማለትም  የደብሩን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ነጥቦች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ  የ2021 በጀት ዓመት ማጽደቅ  የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ማከናወን መሆናቸውን ገልጠዋል ። የጠቅላላ ጉባኤ የምርጫው......

Read More