Blog


29
Sep 2022
የ፳፻፲፭ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በሄልሲንኪ ፊንላንድ በደማቅ ሥነሥርዓት ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ማርያም አቢያተ ክርስቲያን በአንድነት የመስቀልን ደመራ በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት አከበሩ። በዕለቱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ካህናት እና ምእመናን ከመላዋ ፊንላንድ የመጡ በአንድነት በቦታው ተገኝተዋል።በተጨማሪም በክብር እንግድነትም የሂልሲንኪ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሊዮ ዋና ፀሐፊ ቀሲስ ላዛርዩስ ተገኝተው ለሕዝበ ክርስቲያኑ መልእክት አስተላልፈዋል።   በመጨረሻም የሁለቱ አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድና ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ አንገሶም ዕቁባይ ትምህርት ከሰጡ በኋላ ደመራው ተለኩሶ ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ዝማሬ ዘምረው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖአል።...

Read More


21
Aug 2022
የደብረ ታቦር በዓል በሄልሲንኪ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ

በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የደብረ ታቦር በዓል የደብሩ ሕጻናት አዳጊ ልጆች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል ። የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይሜኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት በተለይ በዝርወቱ ዓለም ተወልደው የሚያድጉ ተተኪው ትውልድ የበዓላትን አከባበር እንዲሁም ትውፊታዊውንም ቅብብል በተግባር ያውቁ ዘንድ እንዲያስችል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። ወላጆችም ለዚሁ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብለዋል ። በቀጣይ የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመትም እንዲሁ በደሜቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከበር ጠቁመዋል። በተያያዘ ዜና ነሐሴ 14 /2014 ዓ.ም በታምፔሬ ከተማ በታምፔሬ የሚገኙ የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጽዋዕ ማኅበር አባላት......

Read More


25
Jul 2021
የአገልግሎት ምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ

በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለወ/ሮ አለማች ገብረ ሚካኤል የአገልግሎት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጠ። በሀገረ ፊንላንድ ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ በመንፈሳዊ አገልግሎት በማኅበራዊ አገልግሎት ለሚታውቁት ወ/ሮ አለማች ፣ ሐምሌ ፲፯/፳፻፲፫ ዓ.ም በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት የምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ ። በዕለቱም በመርሐግብሩ የታደሙት ምእመናን ወ/ሮ አለማች በሀገረ ፊንላንድ በስደት ለሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ያዘነውን በማጽናናት ፣ በመጠየቅ የሀገረ ፊንላንድንም ሥርዓተ ሀገሩንም በማለማመድ ከፍተኛ አገልግሎት ማበርከታቸውን ተናግረዋል ። ወ/ሮ አለማች በተለይ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከታላቁ ካህን አባታቸውና ከለጋሷ እናታቸው የወረሱትን በጎ ተግባር ስደቱ ተጽእኖ ሳይፈጥርባቸው ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን......

Read More


26
Dec 2020

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንድኔቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ቤተክርስቲያን እሑድ ታኅሣሥ 11 ቀን /2013 (20.12.2020) በርቀት በስካይፔ ባካሄደው ዓመታዊ የአጥቢያ ምእመናን መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፈረንጆቹ ከ2021 ዓ.ም ጀምሮ በደብሩ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ቤተክርስቲያኗን የሚያገለግሉ አዲስ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላ ምርጫን አካሄዷል። ጠቅላላ ጉባኤውን በጸሎት ክፍተው የመሩት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ የዕለቱን አጀንዳዎች ማለትም  የደብሩን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ነጥቦች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ  የ2021 በጀት ዓመት ማጽደቅ  የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ማከናወን መሆናቸውን ገልጠዋል ። የጠቅላላ ጉባኤ የምርጫው......

Read More


14
Sep 2020
የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ እረፍት በደማቅ ሥነ ሥርዓት በሄልሲንኪ ተከበረ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንድኔቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍት ክብረ በዓል ነሐሴ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ተከበረ። በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያና የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን ተገኝተዋል። በዓሉ ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት የጻድቁን ገድል በመተርጎም የተጀመረ ሲሆን፤ ከመንፈቀ ሌሊት ጀምሮ ማኅሌት ተቋሟል። ከማኅሌቱ በመቀጠል እሑድ ጠዋት የቅዳሴ ጸሎት ከተከናወነ በኋላ በዓሉ አስመልክቶ በደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ ትምህርት ተስጥቷል። በትምህረቱም ላይ የደብሩ አስተዳዳሪ ባስተላለፉት መልእክት የጻድቁ አቡነ ተክለ......

Read More


26
Aug 2020

 በፊላንድ ታምፔሬ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓተ ቅዳሴ ተከናወነ። የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ኪዳነ ምሕረት የጽዋዕ ማኅበር ጥቅምት 1/2012 ዓ ም የተቋቋመ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ( 22/8/2020 ) Tuomiokirkokatu 27 ላይ በሚገኘው የፊላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቅዳሴው አገልግሎት የተመራው  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በስዊድንና ስካንዲናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ እንዲሁም በፊላንድ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ ሰላም መድኅንያዓለም ቤተክርስቲያን ምክትል አስተዳዳሪ  ቀሲስ አንገሶም  ዲያቆናት አማካኝነት የተፈጸመ ሲሆን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን ጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት መዘምራን እንዲሁም ከፊላንድ ከተለያየ......

Read More


04
Aug 2020
የልጆችና የወላጆች ልዩ መርሐ ግብር ተካሄደ

በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የተጋጀው ልዩ የልጆችና የወላጆች መርሐ ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ ተካሄደ! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንዲናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ልዩ የልጆችና የወላጆች መርሐ ግብር ቅዳሜ ሐምሌ 25/11/2012 በሰሜናዊ ሄልስንኪ በተለምዶ ሃጋ አካባቢ በሚገኘው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ተከናውኗል። በአይነቱ ልዩ የሆነው የልጆች እና የወላጆች መርሐ ግብርን በጸሎትና ያስጀመሩት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ነበሩ። በመቀጠልም መርሐ ግብሩን ያዘጋጁት በጽጌ......

Read More


26
Apr 2020
ቤተ ክርስቲያኗ ልጆቿ ምእመናን  ያሉበትን ሁኔታ የሚከታተል ኮሚቴ ማዋቀሯ ተገለጠ

በስዊድንና እስካንድናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘው በኮረና ቫይረስ እየቀጠፈ ያለው ሕዝብ በዝርወት ከሚከኙት መካከል ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ተጠቃሾች መሆናቸው የሚታወቅ በመሆኑ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት በሥሯ አገልግሎት የሚያገኙትን በመላዋ ፊንላንድ የሚገኙትን ምእመናንን ጤንነት እና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የመረዳዳት በጎ ተግባር የሚያስተባብር ኮሚቴ ማዋቀሯን የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ለማ በሱፍቃድ ገለጹ፡፡ ኮሚቴው የአጥቢያው ምእመናን በዚህ ቫይረስ ቢያዙ እንኳን አስፈላጊውን ማኅበራዊ ሥነ ልቡናዊና ተመሳሳይ እገዛዎችን ለማድረግ እንደሚያስተባብር ተጠቁሟል ፡፡ ኮሚቴው ከሄልሲንኪ ውጪ ባሉት ምእመናን ባሉባቸው ከተሞችም የመረዳዳት አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርግበትን አቅጣጫም ማስቀመጡን ታውቋል፡፡......

Read More


21
Jan 2020
በፊንላንድ ሄልሲንኪ የጥምቀት በዓል  በታላቅ  ድምቀት ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ጥር  11 /አሥራ አንድ የሚከበረው የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን  በተለየ  ሃይማኖታዊ ድምቀት ተከብሯል። የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡን ተከትሎ  ዘንድሮ  ሥርዓቱን በጠበቀና በደመቀ  መልኩ   ታቦተ ሕጉ በምእመናን ታጅቦ ከበዓሉ ዋዜማ  በሚከበረው የከተራ በዓል ጊዜያዊ ማረፊያው ጉዞ አድርጎል:: ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ድምቀት የተጀመረው የጥምቀት በዓሉ ሌሊቱን በካህናቱ አገልግሎት አድሮ ከሌሊቱ 10 /አሥር ሰዓት/ ጀምሮ የቅዳሴ ሥነ ሥርዓቱ ቀጥሏል። የቅዳሴው ሥርዓት ከተፈፀመ በኋላ ባሕረ ጥምቀቱ ተባርኮ ሕዝበ ክርስቲያኑም ጠበል ተረጭቷል። የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ  ቀሲስ......

Read More


29
Aug 2019
በዓለ እረፍቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ

በስዊድንና እካንድናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በዓለ እረፍቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ነሐሴ 18 እና 19/2011 ዓ.ም በድማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ። በበዓሉ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የተገኙ ሲሆን ሌሎችም ከ አውሮጳ ከተለያዩ አድባራት የተጋበዙ ሊቃውንትም በበዓሉ ተገኝተዋል ። ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ከበዓሉ ቀደም ብለው ሄልሲንኪ የገቡ ሲሆን ከፊንላንድ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሊዮ ጋር የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርትሲያን ለቤተ ክርስቲያናችን እስካሁን ላደረገችውና እያደረገች ላለው ትብብር አመስግነዋል። ወደፊትም ለአስፈላጊው አገልግሎት ሁሉ እንዲተባበሩ ጥሪ ከማቅረባቸው በተጨማሪም የጋራ በሆኑ አገልግሎቶች ተባብሮ መሥራትን በተመለከተ በማንሳት ውይይት አድርገዋል ።......

Read More