Daily Archives: December 26, 2017


26
Dec 2017
ስለ እመቤታችን ልደት (ለሕፃናትና ዠማሪዎች)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት ሰነበታችኁ? እግዚአብሔር ይመስገን ደኅና ነን አላችኁ? አሜን፡፡ እኔም በጣም ደኅና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ልጆች! ባለፈው ጊዜ ስለምን እንደተማማርን ታስታውሳላችኁ? አቤል እና ቃየን ስለሚባሉ ኹለት ወንድማማቾች አይደል? ጐበዞች! ትክክል ናችኁ፡፡ ዛሬ ደግሞ ኹላችንም ስለምንወዳት ስለ እናታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት እነግራችኋለኹ፡፡ ለመስማት ዝግጁ ናችኁ አይደል? ጐበዞች፡፡ እግዚአብሔር ዕውቀቱን ይግለጥልን፡፡ አሜን!!! የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አባት ኢያቄም ይባላል፡፡ እናቷ ደግሞ ሐና ትባላለች፡፡ ኢያቄምና ሐና እግዚአብሔርን በጣም የሚወዱትና በሕጉ የሚኖሩ ደጋጐች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሐና መካን ስለነበረች ኹለቱም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ዕለት......

Read More


26
Dec 2017
የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቫሳ ከተማ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የቤተክርስቲያን ሰሜን ምዕራብ አውሮፖ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ቫሳ ከተማ የሚኖሩ ምእመናን ባቋቋሙት የቅዱስ ገብርኤል ጽዋዕ ማኅበር አስተባባሪነት ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓል ባሳለፍነው ቅዳሜ ታኅሣሥ 14 ቀን 2010 ዓ.ም በሥርዓተ ቅዳሴና በጉባኤ ተከብሮ ውሏል። በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የሚያገለግሉ ካህናት፤ እንዲሁም ከደብሩ መዘምራን የተወሰኑት ለዚሁ አገልግሎት ከአርብ ጃምሮ በቦታው በመድረስ ቫሳ በሚገኘው የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለምእመናኑ ቅዳሴ ትምህርትና ምክር አገልግሎት ተሰጥቷል። በተለይም ከቅዳሴው በኋላ በተካሄደው ጉባኤ ላይ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ በዓሉን የተመለከተና ከምእመናን ሕይወት ጋር በማያያዝ ሰፋ......

Read More