Blog5 Right Sidebar

30
Apr 2016
ቀዳሚት ሥዑር

በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አድሮ የዋለባት ዕለት በመሆኗ «ቀዳሚት ሥዑር » ትሰኛለች፡፡ ቀዳሚት ሥዑር የተባለችው በዓመት አንድ ቀን ስለ ሚጾምባት ነው፡፡ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያም ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንስተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ። አልቀመሱም ፡፡ አምላካቸው በመቃብር ስላደረ ዕለቷን ሞቱን በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም ውለዋል። ከቅዱሳን ሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን በመጾምና በመጸለይ ዕለቷ እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆች የተቻላቸው ከዓርብ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ ቀምሰው ቅዳሜን በመጾም/ በማክፈል ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ ለምን......

Read More


የስቅለት በዓል ዛሬ በደብራችን በድምቀት ተከብሮ ዋለ
April 30, 2016

የስቅለት በዓል ዛሬ በደብራችን በድምቀት ተከብሮ ዋለ

የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል ዛሬ በደብራችን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ በዕለቱንም ከጠዋት ጀምሮ በርካታ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ጌታችን ስለኛ ብሎ የተቀበለውን መከራና ስቃይ...


ዕለተ ዓርብ(ስቅለት)
April 28, 2016

ዕለተ ዓርብ(ስቅለት)

“አንዱ ስለሁሉ ሞተ” (2ቆሮ 5÷14) የስሞነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያናችን ልዩ ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን ልዩ ነው፣ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁትን ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሣ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ...


የፀሎተ ሐሙስ በዓል በቤተክርስቲያናችን ተከብሮ ዋለ
April 28, 2016

የፀሎተ ሐሙስ በዓል በቤተክርስቲያናችን ተከብሮ ዋለ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ የሚከናወነው የፀሎተ ሐሙስ የእግር አጠባ እና የጸሎተ ቅዳሴት ሥነ ሥርዓት ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ የደቀ መዛሙርቱን...


ዕለተ ሐሙስ
April 27, 2016

ዕለተ ሐሙስ

ይህ ዕለት በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነው፡፡ ሕፅበተ እግር  ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ወንጌሉ እንዲህ ይላል ‹‹እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው...


ሰሙነ ሕማማት  ረቡዕ - የምክር ቀን
April 26, 2016

ሰሙነ ሕማማት ረቡዕ – የምክር ቀን

ለምን የምክር ቀን ተባለ? ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን...


ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ የጥያቄ ቀን
April 26, 2016

ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ የጥያቄ ቀን

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት...


ሰሙነ ሕማማት ሰኞ - አንጾሖተ ቤተ መቅደስ  እና መርገመ በለስ
April 25, 2016

ሰሙነ ሕማማት ሰኞ – አንጾሖተ ቤተ መቅደስ እና መርገመ በለስ

በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል እንደተገለጠልን ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ በምትባል መንደር ያድርና በማግስቱም ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ተራበ ፡፡/ማር. 11.11-14/ ቅጠል ያላትን በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፣ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም...


ቤተ ክርስቲያናች በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ  አስመረቀች
April 24, 2016

ቤተ ክርስቲያናች በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ አስመረቀች

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክርለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ  አስመረቀች። በድረ ገጽ ስም www.teklehaymanot.fi በመባል የተሰየመውን ድረ ገጽ መርቀ የከፈቱት የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ሲሆኑ የተሠራው ሥራ እጅግ ዘመናዊና...


ሆሣዕና ዕለት ከተፈጸሙት ተግባራት ምን እንማራለን?
April 24, 2016

ሆሣዕና ዕለት ከተፈጸሙት ተግባራት ምን እንማራለን?

ፍጹም ትህትናን ነብዩ ኢሳይያስ ”እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር”(ኢሳ 6፥1)። ብሎ የተናገረለት የጌቶች ጌታ የንጉሦች ንጉሥ የሆነ አምላክ ራሱን ዝቅ አድርጎ በአህያ ጀርባ መቀመጡ ፍጹም ትህትናን ያስተምረናል።...


Social Icons

Calendar

April 2024
M T W T F S S
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
2930  

instagram

    flickr

    instagram