Blog5 Right Sidebar

26
Aug 2016
አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍት የዋዜማ በዓል በድምቀት ተከበረ!

በፊላንድ ሄልሲንኪ አሉንኩላን ቤተክርስቲያን የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍታቸውን አስመልክቶ የዋዜማ ጉባኤ የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ፤ ተጋባዥ እንግዶች መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ከስዊድን) ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ(ከኢትዮጵያ) መምህር ፍቃዱ ሣህሌ(ከኢትዮጵያ) ፣ የሰንበት ት/ቤቱ መዘምህራን እና ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ተከብሯል፡፡ ሕጻናትም በፕሮግራሙ ላይ ዝማሬን አቅርበዋል። በነገውም ዕለት ከቀኑ 12:00 ሰዓት እስከ 18:00 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 22:00 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የአዳር መንፈሳዊ አገልግሎቶች በሶፊያ የባህል አዳራሽ እንደሚቀጥልም ተገልጾዋል። በዋዜማ ሌሊቱን በማህሌት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በጋራ በመሆን መንፈሳዊ አገልግሎት ይቀጥላል።...

Read More


በቫሳ ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዳሴና የሥርዐተ ጥምቀት አገልግሎት ተሰጠ
August 18, 2016

በቫሳ ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዳሴና የሥርዐተ ጥምቀት አገልግሎት ተሰጠ

በቫሳና አካባቢው ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እሑድ ነሐሴ 8 2008 ዓ.ም. ከሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ወደ ስፍራው በተጓዙ አገልጋዮች አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዳሴና የሥርዓተ ጥምቀት አገልግሎት ተከናውኗል፡፡ በዕለቱ በተካሄደው  መንፈሳዊ...


ጾመ ፍልሰታ
August 05, 2016

ጾመ ፍልሰታ

ጾመ ፍልሰታ ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጉም ስናነሣ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጣ /የተገኘ/ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ ከምድር ከመቃብር መለየት፣ ማረግ፤ ወደ ላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ያመለክታል፡፡ በዚህ መሠረት ጾመ ፍልሰታ በአጠቃላይ የእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋዋን ከመቃብር መለየትና ወደ ገነት ማረጉን...


መወቀር
July 24, 2016

መወቀር

ክርስትና ሰዉነት ለክርስቶስ ማደሪያ መቅደስነት የተሠራበት የድኅነት መንገድ ነው፡፡ሰው በነፍሱ ወይም ከትንሣኤ በኋላ ባለው ሕይወቱ ብቻ ሳይሆን በዚህ ምድር በሚኖርበት ጊዜም ሰዉነቱ የክርስቶስ ማደሪያ መቅደስ፣ኅሊናዉ ቃሉ የተቀረጸበት ጽላት፣ ልቡናዉም የበጎ ነገር ሁሉ ማደሪያ ታቦት እንዲሆን...


በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ
May 22, 2016

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር ግንቦት 13/2008 ዓ.ም (May 21 2016) “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም አንተው” በሚል መሪ ቃል ልዩ የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ። ዐውደ ርእዩን መርቀው የከፈቱት የፊኒሽ ኦርቶዶክስ...


የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት ከአንድ ቀን  ዐውደ ርእይ ጋር ለማክበር ዝግጅት መጨረሱን አስታወቀ
May 12, 2016

የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት ከአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ጋር ለማክበር ዝግጅት መጨረሱን አስታወቀ

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር ግንቦት 13/2008 ዓ.ም(May 21 2016) የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት እንደሚከበር የደብሩ ጽ/ቤት አስታወቀ። በዓሉ በደብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚከበር የተገለጸ ሲሆን በዕለቱ “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም...


ዳግም ትንሣኤ (ለሕፃናት)
May 08, 2016

ዳግም ትንሣኤ (ለሕፃናት)

ጌታችን በተነሣበት ዕለት የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ተሰብስበው ሳለ ጌታችን በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን “አላቸው፡፡ የነበሩበት ቤት በሩም መስኮቱም ተቆልፎ ስለነበር ደቀ መዛሙርቱም በጣም ደነገጡ፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም “አትፍሩ እኔ አምላካችሁ ነኝ” ብሎ የተወጋ ጎኑን...


የሄልሲን ደብረ አሚን አቡነ የተክለሃይማኖት ደብር በፊላንድ መንግስት እውቅና አገኘ!
May 05, 2016

የሄልሲን ደብረ አሚን አቡነ የተክለሃይማኖት ደብር በፊላንድ መንግስት እውቅና አገኘ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር በፊላንድ መንግስት በቤተክርስቲያን ደረጃ ተመዝግቦ እውቅና መሰጠቱን የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ አስታወቁ። የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት...


ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
May 02, 2016

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ ✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል-ማዕዶት ማለት መሻገር, ማለፍ ማለት ነው. በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን , ከሞት ወደ ሕይወት, ከሲኦል ወደ ገነት, ከሃሳር ወደ ክብር...


Social Icons

Calendar

April 2024
M T W T F S S
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
2930  

instagram

    flickr

    instagram