22
Jan 2017
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል የሕፃናትና አዳጊ ንዑስ ክፍል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ እሑድ ታኅሣሥ 30 ቀን 2009 ዓ.ም (January 8, 2017) ከሰዓት በኋላ ልዩ የሕጻናት እና የአዳጊ ልጆች መርሐ ግብር ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ መጀመሪያ ላይ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ በተላለፈው መልእክት ሕፃናትና አዳጊ ልጆች የነገ የቤተ ክርስቲያናችን ተረካቢዎች በመሆናቸው ትኩረት፣ ፍቅርንና ጊዜን ሰጥተን መሥራት የሚጠበቅብን መሆኑን እና ጥሩ ምሳሌ መሆን ከሁሉም ምእመናን የሚጠበቅ መሆኑ ተገልጿል። ይህን መሰል ልዩ መርሐ ግብር ለልጆች......
Read More
07
Jan 2017
እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደህና ናችሁ? ዛሬ ስለጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት /ገና በዓል/ እንነግራችኋለን፡፡ በደንብ ተከታተሉን፡፡ እሺ? ልጆች በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ፡፡ አውግስጦስ ቄሳር የተባለ ንጉሥ ሰው ሁሉ ይቆጠር ዘንድ አዘዘ፡፡ በትእዛዙ መሠረትም ሰው ሁሉ ሊቆጠር ወደየትውልድ ከተማው ሄደ፡፡ ዮሴፍና እመቤታችንም ሊቆጠሩ ከናዝሬት ወደ ትውልድ ሥፍራቸው ወደ ቤተልሔም ሄዱ፡፡ በቤተልሔም ሳሉም እመቤታችን የምትወልድበት ቀን ደረሰ፡፡ በዚያ ሥፍራም ብዙ እንግዳ ስለነበር እነ ዮሴፍ የሚያርፉበት ቦታ አላገኙም ነበር፡፡ ማደርያም ስላልነበራቸው በከብቶች ማደርያ በበረት ውስጥ እመቤታችን ልጅዋን ወለደችው፡፡ በጨርቅ ጠቅልላ እዛው በበረት ውስጥ አስተኛችው፤ በዚያ ሀገር ይኖሩ የነበሩ እረኞችም ሌሊት ከብቶቻቸውን ይጠብቁ ነበር፤......
Read More
07
Jan 2017
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ!!! ከጌታችን ከልደቱ ያገኘነው ምንድን ነው? ዳግም ልደት በአዳም በደል ምክንያት አጥተነው የነበረው ልጅነታችንን ክርስቶስ በልደቱ ዳግመኛ እንደመለሰልን ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 1፥12 በማለት ገልጾታል። ሰላም በጌታችን ልደት ለዓለም ሁሉ የሚሆን ዘላለማዊ ሰላም ተገኝቷል። ይህም “ክብር እግዚአብሔር በሰማያት ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጐ ፈቃድ” እያሉ ቅዱሳን መላእክት በመዘመራቸው ተረጋግጧል። ሉቃ 2፥14። ስለዚህ በክርስቶስ ያገኘነው እውነተኛ ሰላም በእኛ ጸንቶ እንዲኖር ዘወትር በጾምና በጸሎት እየተጋን ስለሰላም የምንማፀን ሆነን ልንገኝ ይገባል። ሰላም የክርስትና መታወቂያ አርማ......
Read More
03
Jan 2017
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 24 ቀን የሚውለውን የጻድቁ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ቲኩሪላ በሚገኘው የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተከበረ። በዓሉ ታኅሣሥ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ፣ የደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ ሕጻናት፣ ከሄልሲንኪና እና ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ምእመናን እና ምእመናት እንዲሁም በፊንላንድ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት ተከብሯል። በዓሉ ዓርብ ምሽት በጸሎት ከተጀመረ በኋላ የአቡነ ተክለ......
Read More
30
Nov 2016
29
Sep 2016
በፊንላንድ ሄልሲንኪ ከተማ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን አደባባይ. /ሜዳ / ላይ በተካሄደው የደመራ ሥነ ሥርዓት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ፣ የሄልሲንኪ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሪትቫ ቪልያነን ፣ የደብሩ ዲያቆናት ፣ የሄልሲንኪ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት ዲያቆናት እና ምእመናን ፣ ጥንግ ድርብ የለበሱ የደብሩ መዘምራን፣ ሕጻናት፣ ከሄልሲንኪና ከአጎራባች ከተሞች የመጡ ምእመናን፣ የባህል እና የሌሎች ተቋማት ሓላፊዋች ፣ጋዜጠኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ከ 17፡30 – 20፡30 በተካሄደ የመስቀል ደመራ ሥነ ሥርዓት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። ሥነ......
Read More
24
Sep 2016
በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ የመስቀል ደመራን በዓል በሄልሲንኪ ከተማ የዮሐንስ ቤ/ክ አጠገብ በሚገኘው (korkeavuorenkatu 12) አደባባይ/ሜዳ/ ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ከ17፡30– 20፡30 ፣ የደመራ ሥነ ሥርዓት በማከናወን እንደሚያከብር ተገለጸ። የደመራ ሥነ ሥርዓቱ የደብሩ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን፣ ሕጻናት፣ በሄልሲንኪና አጎራባች ከተሞች የሚገኙ ምእመናን፤ ተጋባዥ ካህናት፣ ዲያቆናት ፣ የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሓላፊዎች ፣ የከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት እና ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እንደሚከናወን ታውቋል፡፡ የመስቀል ደመራ በዓል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአይሁድ አማካኝነት ተቀብሮ ከነበረበት ቦታ የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት የሆነቸው ንግሥት ዕሌኒ ፣ ደመራ......
Read More
08
Sep 2016
29
Aug 2016
በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖትን የበዓለ ዕረፍታቸውን ዓመታዊ ክብረ በዓል ነሐሴ 22 ቀን 2008ዓ.ም. (28.08.16 እ.ኤ.አ) ፣ ቮሳሪ በሚገኘው የፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሶፊያ ማዕከል በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ፡፡ በበዓሉ ላይ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱ ፈቃድ የደብሩ አስተዳዳሪ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ቀሲስ አንገሶም በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ እና የደብሩ ዲያቆናትና ቀሳውስት መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ከስዊድን) ፣ ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ(ከኢትዮጵያ)፣ መምህር ፍቃዱ ሣህሌ(ከኢትዮጵያ) ፣ እንዲሁም ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ሕጻናትና በፊንላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያና......
Read More
29
Aug 2016
ነሐሴ 21 2008 ዓ.ም. (27.08.16 እ.ኤ.አ) በሶፈያ የባህል ማዕከል ”ኢትዮጵያ ዛሬ (Etiopia tänään)” በሚል መሪ ቃል በሶፍያ የባህል ማዕከል እና በፊኒሽ ኦርቶዶክስ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት ተካሄደ። ዐውደ ጥናቱ የተለያዩ መርሀግብሮችን በማካተት ከቀኑ 12፡00 እስከ 18፡00 ቀጥሎ ውሏል። ከቀኑ 12-14 ሰዓት በዕለቱ በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጋባዥነት ከስዊድን የሉንድ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ታሪክ በሚመለከት ጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ ፣ በቦታው ለታደሙት የጉባኤው ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡ በማስከተልም። ወ/ሪት ፌቨን ትዕግሥቱ “ቱሪዝም በኢትዮጵያ” በተሰኘ ርዕስ የኢትዮጵያን ዋና ዋና......
Read More