Start Blog Type 1 (Full Width Image) and Sidbar

09
Feb 2017
የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሁለት የወረዳ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤቶችን አዋቀረ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የወረዳ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤቶችን አዋቀረ። ሀገረ ስብከቱ የመላው አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሙሴ መቀመጫ በሆነችው በጀርመን ሀገረ በምትገኘው የሮሰልስሃይም ከተማ ጥር 19 እና 20 ቀን 2009 ዓ.ም ጉባኤውን አካሂዷል። በጉባኤው ላይ የአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ በሸንገን ስቴት ውስጥ ባሉ የአውሮፓ ሀገራት ያሉ የሀገረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች እና ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችንም አሳልፏል። ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልእክት በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት እና የቤተ ክርስቲያንን......

Read More


25
Jan 2017
በዓለ ጥምቀት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጥር 13 ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ቲኩሪላ በሚገኘው በፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። በዕለቱ በተያዘው መርሃ ግብር መሠረት ሥርዓተ ቅዳሴው ከተከናወነ በኋላ የባህረ ጥምቀቱ ሥርዓተ ጸሎት ተደርሶ ህዝቡም ጸበል ተረጭቶ የበረከቱ ተካፋይ ሆኗል፡፡በመቀጠልም በደብሩ መዘምራን ዕለቱን የተመለከተ  ያሬዳዊ ዜማ የቀረበ ሲሆን  በመጨረሻም በደብሩ አስተዳዳሪ በመጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ   ትምህርተ  ወንጌል  እና ጸሎተ ቡራኬ ከተሰጠ በኋላ  የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።...

Read More


22
Jan 2017
የልደትን በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የሕጻናት መርሐ ግብር ተካሄደ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል የሕፃናትና  አዳጊ ንዑስ ክፍል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ እሑድ ታኅሣሥ 30 ቀን 2009 ዓ.ም (January 8, 2017) ከሰዓት በኋላ ልዩ የሕጻናት እና የአዳጊ ልጆች መርሐ ግብር ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ መጀመሪያ ላይ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ በተላለፈው መልእክት ሕፃናትና  አዳጊ ልጆች የነገ የቤተ ክርስቲያናችን ተረካቢዎች በመሆናቸው  ትኩረት፣ ፍቅርንና ጊዜን ሰጥተን መሥራት የሚጠበቅብን መሆኑን እና ጥሩ ምሳሌ መሆን ከሁሉም ምእመናን የሚጠበቅ መሆኑ ተገልጿል። ይህን መሰል ልዩ መርሐ ግብር ለልጆች......

Read More


07
Jan 2017
ልደተ ክርስቶስ /የገና በዓል/ - ለሕጻናት

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደህና ናችሁ? ዛሬ ስለጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት /ገና በዓል/ እንነግራችኋለን፡፡ በደንብ ተከታተሉን፡፡ እሺ? ልጆች በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ፡፡ አውግስጦስ ቄሳር የተባለ ንጉሥ ሰው ሁሉ ይቆጠር ዘንድ አዘዘ፡፡ በትእዛዙ መሠረትም ሰው ሁሉ ሊቆጠር ወደየትውልድ ከተማው ሄደ፡፡ ዮሴፍና እመቤታችንም ሊቆጠሩ ከናዝሬት ወደ ትውልድ ሥፍራቸው ወደ ቤተልሔም ሄዱ፡፡ በቤተልሔም ሳሉም እመቤታችን የምትወልድበት ቀን ደረሰ፡፡ በዚያ ሥፍራም ብዙ እንግዳ ስለነበር እነ ዮሴፍ የሚያርፉበት ቦታ አላገኙም ነበር፡፡ ማደርያም ስላልነበራቸው በከብቶች ማደርያ በበረት ውስጥ እመቤታችን ልጅዋን ወለደችው፡፡ በጨርቅ ጠቅልላ እዛው በበረት ውስጥ አስተኛችው፤ በዚያ ሀገር ይኖሩ የነበሩ እረኞችም ሌሊት ከብቶቻቸውን ይጠብቁ ነበር፤......

Read More


Social Icons

Calendar

May 2024
M T W T F S S
 12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
2728293031  

instagram

    flickr

    instagram