Start Blog Type 1 (Full Width Image) and Sidbar

13
Jun 2017
የተመራቂ ተማሪዎች ልዩ መርሃግብር ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰኔ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም (June 11, 2017) ዓ.ም በቀለም ትምህርታቸው ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለተመረቁ ተማሪዎች ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጀ። በመርሃ ግብሩ መጀመሪያ በደብሩ የስብከተ ወንጌል ክፍል ተጠሪ በተላለፈው መልእክት በዘንድሮ ዓመት የተጀመረው ይህ የተመራቂዎች መርሃ ግብር ወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን መንፈሳዊውንም ትምህርት በሰንበት ትምህርት ቤት ተመዝግበው ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ከዛሬ በኋላ ተመራቂዎቹ በእውቀታቸውና በመሳሰለው ሁሉ ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ ቀርቧል ። መርሃ......

Read More


13
May 2017
የትንሣኤና የእመቤታችን የድንግል ማርያም የልደት በዓል ልዩ መርሐ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት  የሕፃናትና አዳጊዎች  ንዑስ ክፍል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓልና የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ሚያዝያ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. (May 7, 2017) ልዩ የሕፃናት እና የአዳጊ ልጆች መርሐ ግብር ተካሄደ።  በመርሐ ግብሩ መጀመሪያ ላይ ከሕፃናት እና አዳጊዎች ንዑስ ክፍል በተላለፈው መልእክት ሕፃናትና  አዳጊ ልጆች የነገ የቤተ ክርስቲያናችን ተረካቢዎች በመሆናቸው ይልቁንም በውጪው ዓለም ለሚገኙ ሕፃናትና አዳጊዎች  የበልጠ ትኩረት በመስጠት  ሃይማኖታቸውን ፣ ቋንቋቸውን እና በጎ ባህላቸውን እንዲያውቁ እና......

Read More


13
Apr 2017
የሆሣዕና በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሚያዚያ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. የሆሣዕና በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ። በዕለቱም በየዓመቱ እንደሚከናወነው ሁሉ ቅዳሴ ሥርዓቱ በተለየ ሁኔታ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት ከተከናወነ በኋላ በቀሲስ ዶክተር አምሳሉ ተፈራ ስለ ሆሣዕና በዓል አጠር ያለ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ የሆሣዕና በዓል ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አዕሩግም ሕፃናትም ‹‹ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፣ሆሣዕና በአርያም›› እያሉ ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል መሆኑን፤ ‹ሆሣዕና› የሚለው ቃል ‹ሆሼዕናህ› ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተወሰደ ሲሆን ፣......

Read More


13
Apr 2017
በሶፊያ ባህል ማዕከል ልዩ ዐውደ ጥናት ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እና በፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሶፊያ ባህል ማዕከል ትብብር ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. በሶፊያ የባህል ማዕከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትን እና የቅዱስ ያሬድን ዜማ በሚመለከት ልዩ ዐውደ ጥናት ተካሄደ፡፡ በዐውደ ጥናቱም ላይ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፈቃድ፣ የአጥቢያው ምእመናን፣ የፊንሽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች እና የሀገሪቱ ዜጎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በመጀመሪያ ገዳማዊ ሕይወት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሚል ርዕስ የገዳማዊ ሕይወት አጀማመር፣ ያበረከተው አስተዋጽዖ እና......

Read More


Social Icons

Calendar

May 2024
M T W T F S S
 12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
2728293031  

instagram

    flickr

    instagram