Daily Archives: March 28, 2016


28
Mar 2016
እናትና አባትህን አክብር (ለሕፃናት)

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች ደህና ናችሁ በዛሬው የመጀመሪያ ጽሑፋችን እናትና አባትን ስለማክበር እንማማራለን ስለዚህ በደንብ ተከታተሉን፡፡ ከነብየ እግዚአብሔር ሙሴ የኦሪት መጻህፍት መካከል አንዱ በሆነው በኦሪት ዘዳግም 5÷16 ላይ እናትና አባትን ስለማክበር እንድህ በማለት ተናተናግሯል ፡- “እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፣ መልካምም እንዲሆንልህ እናትና አባትህን አክብር፡፡” ዘዳግም 5÷16 ልጆች ከአሥርቱ ትዕዛዛት መካከል አንዱ እናትና አባትህን አክብር የሚለው ነው፡፡ እግዚአብሔር እናትና አባታችንን ካከበርን በምድር ላይ ስንኖር ዕድሜያችን ረዥም እንደሚሆንና፤ በዚህ ዕድሜያችንም መልካም የሆነ ነገር እንደሚያደርግልን ቃል ገብቶልናል፡፡ ለእናትና ለአባታችን ስንታዘዝ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚደሰትና እድሜያችንን እንደሚያረዝምልን ሁሉ ካልታዘዝን ደግሞ ያዝንብናል፡፡ እናትና አባቱን የማያከብር፣ ስድብ......

Read More


28
Mar 2016
እኛንም ያድነናል (ለሕፃናት)

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች ? ደህና ናችሁ? እረፍት እንዴት ነው? የዚህ በሁለት ወር ክረምት እረፍታችሁን እንዴት እያሳለፋችሁ ነው? ልጆች ቤተሰባችሁን በመላላክ ሥራ በማገዝ እያገለገላችሁ ነው? በተለይ ደግሞ በቤተክርስቲያን ተገኝታችሁ ትምህርት ቃለ እግዚአብሄርን በመማር በዝማሬ እግዚአብሄርን እያመሰገናችሁ ነው? እንደዚህ ከሆነ በርቱ እሺ እግዚአብሔር የሚወደው እንደዚህ አይነቱን ነው፡፡ እሺ ልጆች ዛሬ ያቀረብንላችሁ ሐምሌ 19 የሚከበረውን ቅዱስ ገብርኤል ስላዳናቸው አንድ እናትና አንድ ልጅ ታሪክ አዘጋጅተንላችኋል በትዕግስት ተከታተሉን እሺ፡፡ የሕፃኑ ስም ቅዱስ ቂርቆስ ሲሆን የእናቱ ስም ደግሞ ቅድስት ኢየሉጣ ትባላለች አባቱ ቆዝሞስ ይባላል፡፡ ሐገሩ ሮም አንጌቤ ነው፡፡ ዲዮቅልጥያኖስ የተባለ ንጉሥ በነገሠበት ጊዜ በ303 ዓ.ም. አብያተ ክርስቲያናትን ማፈራረስ......

Read More