Large Posts

22
May 2016
በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር ግንቦት 13/2008 ዓ.ም (May 21 2016) “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም አንተው” በሚል መሪ ቃል ልዩ የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ። ዐውደ ርእዩን መርቀው የከፈቱት የፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተለያዩ ባህል ተጠሪ ቄስ ቴሙ ቶኦይቪነን ፣ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ አንተነህ ጉደታ በኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም አስተዳዳሪ ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፍቃድ ነበሩ ። እንዲሁም ቄስ ሚካኤል ሰንድቪስት ከቲኩሪላ ፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ ሚስተር ቬሪኮቨ ሌፍ የሄልሲንኪ ከተማ አስተዳደር የአስተዳደር ክፍል የበላይ ሃላፊ፣ አቶ ኤልያስ ሳቦሬ በፊንላንድ የኢትዮጲያ ኮንስላር በክብር እንግድነተ ተገኝተዋል ።......

Read More


12
May 2016
የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት ከአንድ ቀን  ዐውደ ርእይ ጋር ለማክበር ዝግጅት መጨረሱን አስታወቀ

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር ግንቦት 13/2008 ዓ.ም(May 21 2016) የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት እንደሚከበር የደብሩ ጽ/ቤት አስታወቀ። በዓሉ በደብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚከበር የተገለጸ ሲሆን በዕለቱ “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም አንተው” በሚል መሪ ቃል ልዩ የአንድ ቀን አውደ ርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያካሄድ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፍቃድ ገልጸዋል። አውደ ርዕዩም በአራት ትዕይንት የተከፈለ ሲሆን በተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች በደመቀ ሁኔታ እንደሚታጀብ ተገልጾል። በፊንላንድ እና በአጎራባች ሀገሮች አድባራት የምትገኙ ምእመናን የበዓሉ በረከት ተሳታፊ እንድትሆኑና በዕለቱም ዐውደ ርእዩን እንድትጉበኙ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በጻድቁ ስም ጥሪውን ያስተላልፋል። ወስብሐት......

Read More


08
May 2016
ዳግም ትንሣኤ (ለሕፃናት)

ጌታችን በተነሣበት ዕለት የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ተሰብስበው ሳለ ጌታችን በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን “አላቸው፡፡ የነበሩበት ቤት በሩም መስኮቱም ተቆልፎ ስለነበር ደቀ መዛሙርቱም በጣም ደነገጡ፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም “አትፍሩ እኔ አምላካችሁ ነኝ” ብሎ የተወጋ ጎኑን እና የተቸነከሩ እጆቹን አሳያቸው፡፡ እነርሱም ጌታ ከሞት መነሣቱን አመኑ፡፡ ደቀመዛሙርቱንም(ተማሪዎቹንም) ሕዝቡን እንዲያስተምሩ ላካቸው፡፡ በዚህ ዕለት ከ12ቱ ደቀመዛሙርት አንዱ የሆነው ቶማስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ ደቀመዛሙርቱ የጌታን መነሣት እና እነርሱም እነዳዩት ነገሩት፡፡ እርሱ ግን በዓይኔ ካላየሁ አላምንም አለ፡፡ ከስምነት ቀን በኃላ እንደገና ቶማስ አብሯቸው ሳለ በሩ እንደተዘጋ ጌታችን መጣ፣ በመካከላቸውም ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው፡፡ ቶማስ ትንሣኤውን እነደተጠራጠረ ስላወቀ......

Read More


05
May 2016
የሄልሲን ደብረ አሚን አቡነ የተክለሃይማኖት ደብር በፊላንድ መንግስት እውቅና አገኘ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር በፊላንድ መንግስት በቤተክርስቲያን ደረጃ ተመዝግቦ እውቅና መሰጠቱን የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ አስታወቁ። የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር በማኅበር ደረጃ ከ20 አመታት በላይ ማስቆጥሩ ይታወሳል፤ ይሁንና ላለፉት 5 ዓመት በቤተክርስቲያን ደረጃ ተመዝግቦ በፊንላንድ መንግሥት ዘንድ እውቅና ለማግኘት ከፍተኛ ጥረቶች መደረጋቸውን ተገልፇል። እንደ ደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ለማ ገለፃ የተደረጉት ጥረቶች በመጨረሻ ተሳክተው በፊንላንድ ሀገር የመጀመሪያው በሀገሪቱ መንግስት ዘንድ እውቅና የተሰጠው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ተብሎ መመዝገቡን ተናገረዋል።......

Read More


02
May 2016
ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ ✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል-ማዕዶት ማለት መሻገር, ማለፍ ማለት ነው. በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን , ከሞት ወደ ሕይወት, ከሲኦል ወደ ገነት, ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን. ✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል-በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ; ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል. ዮሐ. 20 27-29 ✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል-በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን . ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ;. የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን ✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል-ዕለት ለአዳም የተሰጠው በዚህ......

Read More


30
Apr 2016
ቀዳሚት ሥዑር

በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አድሮ የዋለባት ዕለት በመሆኗ «ቀዳሚት ሥዑር » ትሰኛለች፡፡ ቀዳሚት ሥዑር የተባለችው በዓመት አንድ ቀን ስለ ሚጾምባት ነው፡፡ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያም ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንስተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ። አልቀመሱም ፡፡ አምላካቸው በመቃብር ስላደረ ዕለቷን ሞቱን በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም ውለዋል። ከቅዱሳን ሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን በመጾምና በመጸለይ ዕለቷ እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆች የተቻላቸው ከዓርብ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ ቀምሰው ቅዳሜን በመጾም/ በማክፈል ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ ለምን......

Read More


30
Apr 2016
የስቅለት በዓል ዛሬ በደብራችን በድምቀት ተከብሮ ዋለ

የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል ዛሬ በደብራችን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ በዕለቱንም ከጠዋት ጀምሮ በርካታ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ጌታችን ስለኛ ብሎ የተቀበለውን መከራና ስቃይ እያሰቡ በመጸለይና በመስገድ አሳልፈዋል፡፡ በደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የ5500 ዓመት የዕዳ ደብዳቤያችን የተደመሰሰበት የተወገደበት ፣ የሰው ልጅ የኃጢአት ቀንበር የተሰበረበት፣ የሞትና የጨለማ መጋረጃ የተቀደደበት፣ ፍፁም ፍቅር የተገለጠበት ዕለት መሆኑን አስተምረዋል፡፡ እኛም በየትኛውም ዓለም የምንኖር ምእመናን ከሁሉም በላይ የሚበልጠው ፍቅር ነውና ፍቅርን ገንዘብ እናድርግ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በማያያዝም ነገ ትንሣአኤ......

Read More