Large Posts

28
Apr 2016
ዕለተ ዓርብ(ስቅለት)

“አንዱ ስለሁሉ ሞተ” (2ቆሮ 5÷14) የስሞነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያናችን ልዩ ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን ልዩ ነው፣ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁትን ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሣ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግርፋት ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን የዓመፃ መዝገባችን መገልበጡ እርግጥ የሆነበት ፣ አሳዳጃችን አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነውና፣ ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡ የስቅለት ዓርብ ይባላል የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለም ድኅነት መስዋዕት......

Read More


28
Apr 2016
የፀሎተ ሐሙስ በዓል በቤተክርስቲያናችን ተከብሮ ዋለ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ የሚከናወነው የፀሎተ ሐሙስ የእግር አጠባ እና የጸሎተ ቅዳሴት ሥነ ሥርዓት ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ትህትናን ለደቀመዛሙርቱ ሐዋርያት ያስተማረበት ቀን መሆኑንና እንዲሁም በማግስቱ ዐርብ ስለ ሰዎች ሲል ስለሚቆረሰው ሥጋውና ስለሚፈሰው ደሙ ትምህርት ሰጥተዋል። በመቀጠልም አባታችን የምእመናንን እግር በማጠብ የሕፅበተ እግር ሥርዓትን አከናውነዋል፡፡ አምላካችን እራሱን ዝቅ አድርጎ ያስተማረንን ትህትና እኛ ልንተገብረው ይገባል ብለዋል፡፡ በማያያዝም ነገ ዕለተ ዐርብ የስቅለት በዓል ቀኑን ሙሉ እንደሚከናውን ተገልጿል። ለብርሃነ ትንሣኤው ያድርሰን፡፡  ...

Read More


27
Apr 2016
ዕለተ ሐሙስ

ይህ ዕለት በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነው፡፡ ሕፅበተ እግር  ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ወንጌሉ እንዲህ ይላል ‹‹እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ዐሳብ ካገባ በኋላ ኢየሱስ ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡›› ዮሐ.13፥1-10 የምስጢር ቀን ይባላል ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣......

Read More


26
Apr 2016
ሰሙነ ሕማማት  ረቡዕ - የምክር ቀን

ለምን የምክር ቀን ተባለ? ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ /ማቴ. 26፤1-14፣ ማር. 14፤1-2፣ ቁ 10.11፣ ሉቃ. 22.1-6/ የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ «ከእንግዲህ......

Read More


26
Apr 2016
ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ የጥያቄ ቀን

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ ማቴ.21÷23-25፤ ማር.11÷27፣ ሉቃ.20÷1-8፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡ ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን......

Read More


25
Apr 2016
ሰሙነ ሕማማት ሰኞ - አንጾሖተ ቤተ መቅደስ  እና መርገመ በለስ

በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል እንደተገለጠልን ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ በምትባል መንደር ያድርና በማግስቱም ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ተራበ ፡፡/ማር. 11.11-14/ ቅጠል ያላትን በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፣ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት፡፡ በዚህ ምክንያት ይህ ዕለት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፡፡ ትርጓሜ፤- በለስ የተባለች ቤተ እስ ራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች፣ ሃይማኖትና ምግባር ናት፡፡ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፡፡ እስራኤልን ሕዝበ እግዚአብሔር መባ ልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥ ዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡ በለስ ኦሪት ናት፡- ኦሪትን......

Read More


24
Apr 2016
ቤተ ክርስቲያናች በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ  አስመረቀች

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክርለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ  አስመረቀች። በድረ ገጽ ስም www.teklehaymanot.fi በመባል የተሰየመውን ድረ ገጽ መርቀ የከፈቱት የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ሲሆኑ የተሠራው ሥራ እጅግ ዘመናዊና ሁሉን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ለምረቃ የበቃው ድረ ገጽ የተሰራው በቤተ ክርስቲያኗ መረጃና ግንኙነት ክፍል ሲሆን እስካሁን የአራት ወር ጊዜ እንደፈጀ ታውቋል። በአሁን ሰዓት ገጹ ላይም የዜና እና መርሐ ግብር፣ የህብር ሚዲያ፣ የህጻናት፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች አምዶች አሉት። በምረቃው ላይ ስለ ድረ ገጽ ትንታኔ የሰጠው የመረጃና ግንኙነት ክፍል አገልጋይ ወንድማችን ካቢናድ ተሻገር እንደተናገረ ይህ......

Read More


24
Apr 2016
ሆሣዕና ዕለት ከተፈጸሙት ተግባራት ምን እንማራለን?

ፍጹም ትህትናን ነብዩ ኢሳይያስ ”እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር”(ኢሳ 6፥1)። ብሎ የተናገረለት የጌቶች ጌታ የንጉሦች ንጉሥ የሆነ አምላክ ራሱን ዝቅ አድርጎ በአህያ ጀርባ መቀመጡ ፍጹም ትህትናን ያስተምረናል። በከበረ ቃሉ ”ከእኔ ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ” (ማቴ 11᎓29) እንዳለን የከበረች ትህትናን ከባለቤቱ መማር ይገባናል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለጌታ ትህትና የተናገረውንም ማስተዋል ይገባል ”እርሱ አምላካችን የሁሉ ፈጣሪና የማይመረመረ ክብር ያለው ንጉሥ ሆኖ ሳለ ለክብሩ በሚገባ ባማረና በተንቆጠቆጠ ቤት አልተወለደም ራሱን ዝቅ አድርጎ በበረት ተገኘ እንጂ። በዚህ ዓለም ባለጠግነትና ብዕል ከተትረፈረፈች እናት አልተወለደም......

Read More