11
Mar 2023
በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የቅዱስ ዑራኤል ጽዋዕ ማኅበር ተመሠረተ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እየተገለገሉ የሚገኙ በዩቫስኲላ ከተማ የሚኖሩ ምእመናን መጋቢት ፪/፳፻፲፭ ዓ.ም በቅዱስ ዑራኤል ስም የጽዋዕ ማኅበር መሠረቱ። በዝርወቱ ዓለም የሚኖሩ ምእመናን በየወሩ እየተሰበሰቡ በጋራ በአንድነት በቅዱሳን ስም የጽዋዕ ማኅበር መሥርተው ይጸልያሉ ፣ይማጸናሉ አመቺ በሆነ ጊዜም ቅዳሴ ይቀደስላቸዋል ፣ በዚሁ መሠረት በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የሚገኙ ምእመናን እጣ በመጣል በተደጋጋሚ ቅዱስ ዑራኤል በመውጣቱ በመልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ስም የጽዋዕ ማኅበር ተመሥርቷል ። በዕለቱ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ......
Read More
February 02, 2023
በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጽጌ ሃይማኖት ስንበት ት/ቤት ለተተኪ መዘምራን ሥልጠና ተሰጠ
ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም፥ በስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለጽጌ ሃይማኖት ስንበት ትምህርት ቤት ተተኪ መዘምራን ‹‹ ብላቴናነትን የመቀደስ ጥበብ በቤተ ክርስቲያን ›› በሚል ርእስ...
January 27, 2023
In Helsinki, Finland, the Debre Amin Abune Tekle haimont Church gave a training that took into account the current challenges of our church
On January 24, 2023, in the Diocese of Sweden, Scandinavia and Greek countries, in Helsinki, Finland, Debre Amin Abune Teklehaymont Church, a mandate was held that took into account the cognitive challenge faced by our...
January 25, 2023
በፊንላንድ ሂልስንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ፈተና ታሳቢ ያደረገ ሥልጠና ተሰጠ
ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም፥ በስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ውቅታዊ ፈተና ታሳቢ ያደረገ ሥልጣን ተካሂዷል። በሥልጠናው መርሐ ግብር...
January 22, 2023
በበረዶዋማ ፊንላንድ አገር የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከበረ
የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን፣ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሰሱ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኘበት በድምቀት ተከብሯል። የበዓሉ ሥነ ሥርዓት የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና...
November 01, 2022
ለ፫ተኛ ጊዜ ቅብዓ ሜሮን የማፍላት ሥርዓተ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ እየተከናወነ ይገኛል
በመ/ር አቤል አሰፋ (ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ) በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን...
September 29, 2022
የ፳፻፲፭ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በሄልሲንኪ ፊንላንድ በደማቅ ሥነሥርዓት ተከበረ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ማርያም አቢያተ ክርስቲያን በአንድነት የመስቀልን ደመራ በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት አከበሩ። በዕለቱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን...
August 21, 2022
የደብረ ታቦር በዓል በሄልሲንኪ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ
በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የደብረ ታቦር በዓል የደብሩ ሕጻናት አዳጊ ልጆች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል ። የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይሜኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ በበዓሉ...