22
Jan 2023
የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን፣ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሰሱ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኘበት በድምቀት ተከብሯል። የበዓሉ ሥነ ሥርዓት የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሆኑት በመልአከ አሚን የተመራ ሲሆን፤ በዓሉን የተመለከ ትምህርት ከኢትዮጵያ በመጡት በዲያቆን ታደሰ ወርቁ ትምህርት ተሰጥቷል። በፊንላንድ ተወልደው ያደጉ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት የጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ተተኪ መዘምራንም በዓሉን የሚያዘክረውን ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል።...
Read More
November 01, 2022
ለ፫ተኛ ጊዜ ቅብዓ ሜሮን የማፍላት ሥርዓተ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ እየተከናወነ ይገኛል
በመ/ር አቤል አሰፋ (ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ) በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን...
September 29, 2022
የ፳፻፲፭ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በሄልሲንኪ ፊንላንድ በደማቅ ሥነሥርዓት ተከበረ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ማርያም አቢያተ ክርስቲያን በአንድነት የመስቀልን ደመራ በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት አከበሩ። በዕለቱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን...
August 21, 2022
የደብረ ታቦር በዓል በሄልሲንኪ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ
በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የደብረ ታቦር በዓል የደብሩ ሕጻናት አዳጊ ልጆች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል ። የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይሜኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ በበዓሉ...
July 25, 2021
የአገልግሎት ምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ
በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለወ/ሮ አለማች ገብረ ሚካኤል የአገልግሎት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጠ። በሀገረ ፊንላንድ ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ በመንፈሳዊ አገልግሎት በማኅበራዊ አገልግሎት ለሚታውቁት ወ/ሮ አለማች ፣ ሐምሌ ፲፯/፳፻፲፫ ዓ.ም በሄልሲንኪ...
December 26, 2020
ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ ተካሄደ ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንድኔቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ቤተክርስቲያን እሑድ ታኅሣሥ 11 ቀን /2013 (20.12.2020) በርቀት በስካይፔ ባካሄደው ዓመታዊ የአጥቢያ ምእመናን መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፈረንጆቹ ከ2021...
September 14, 2020
የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ እረፍት በደማቅ ሥነ ሥርዓት በሄልሲንኪ ተከበረ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንድኔቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍት ክብረ በዓል ነሐሴ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ተከበረ። በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያና...
August 26, 2020
በፊንላንድ ታምፔሬ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓተ ቅዳሴ ተከናወነ
በፊላንድ ታምፔሬ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓተ ቅዳሴ ተከናወነ። የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ኪዳነ ምሕረት የጽዋዕ ማኅበር ጥቅምት 1/2012 ዓ ም የተቋቋመ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ( 22/8/2020 ) Tuomiokirkokatu 27...