07
Apr 2016
”ወበጽርሑሰ ኵሉ ይብል ስብሐት እግዚአብሔር ያስተጋብኦ ለማየ አይኅ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል እግዚአብሔር የጥፋት ውሃን ሰብስቧልና” መዝ ፳፰፥፱ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በዚህ መዝሙሩ ላይ፦ ምዕመናን ለአምላካቸው የአምልኮ መገለጫ የሆኑትን ምስጋናና ስግደት ሊያደርጉ እንደሚገባቸው በመጀመሪያዎቹ ስንኞች ላይ አስፍሯል፦ ”በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ” – እንዲል። በሚቀጥሉት ስንኞች ደግሞ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ አምላክ እንደሆነ ሰብኳል። ”የክብር አምላክ አንጐደጐደ” በማለት በብዙ ምሳሌ አስተምሯል፤ የሊባኖስ ዝግባን፣ ውሃን፣ እሳትን፣ የቃዴስን ምድረ በዳ እየጠቀሰ ተናግሯል። ይህ ሁሉ የእስራኤላውያን የአምልኮ ታሪክና የእግዚአብሔርን ተአምራት የሚያስታውስ ነው፤ ይህውም በምድረ በዳ እና በመሳፍንት ዘመን ሁሉ የነበረው ነው፦ ውሃውን ያለ ግድብ ሲያቆም፣ ከጭንጫ ሲያፈልቅ፣......
Read More