Daily Archives: July 24, 2016


24
Jul 2016
መወቀር

ክርስትና ሰዉነት ለክርስቶስ ማደሪያ መቅደስነት የተሠራበት የድኅነት መንገድ ነው፡፡ሰው በነፍሱ ወይም ከትንሣኤ በኋላ ባለው ሕይወቱ ብቻ ሳይሆን በዚህ ምድር በሚኖርበት ጊዜም ሰዉነቱ የክርስቶስ ማደሪያ መቅደስ፣ኅሊናዉ ቃሉ የተቀረጸበት ጽላት፣ ልቡናዉም የበጎ ነገር ሁሉ ማደሪያ ታቦት እንዲሆን የተዘጋጀ ነዉ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ‹‹ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?… ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ›› /1ኛ ቆሮ 6፤ 13- 19/ ሲል እንደገለጸልን ሰዉነታችን ለእኛ ፍላጎት ማከማቻነት የተዘጋጀ ቁምሳጥን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም የተሰጠን ቅዱስ ንዋይ ነው፡፡ ሐዋርያዉ......

Read More