Daily Archives: May 22, 2016


22
May 2016
በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር ግንቦት 13/2008 ዓ.ም (May 21 2016) “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም አንተው” በሚል መሪ ቃል ልዩ የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ። ዐውደ ርእዩን መርቀው የከፈቱት የፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተለያዩ ባህል ተጠሪ ቄስ ቴሙ ቶኦይቪነን ፣ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ አንተነህ ጉደታ በኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም አስተዳዳሪ ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፍቃድ ነበሩ ። እንዲሁም ቄስ ሚካኤል ሰንድቪስት ከቲኩሪላ ፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ ሚስተር ቬሪኮቨ ሌፍ የሄልሲንኪ ከተማ አስተዳደር የአስተዳደር ክፍል የበላይ ሃላፊ፣ አቶ ኤልያስ ሳቦሬ በፊንላንድ የኢትዮጲያ ኮንስላር በክብር እንግድነተ ተገኝተዋል ።......

Read More