Daily Archives: May 12, 2016


12
May 2016
የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት ከአንድ ቀን  ዐውደ ርእይ ጋር ለማክበር ዝግጅት መጨረሱን አስታወቀ

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር ግንቦት 13/2008 ዓ.ም(May 21 2016) የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት እንደሚከበር የደብሩ ጽ/ቤት አስታወቀ። በዓሉ በደብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚከበር የተገለጸ ሲሆን በዕለቱ “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም አንተው” በሚል መሪ ቃል ልዩ የአንድ ቀን አውደ ርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያካሄድ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፍቃድ ገልጸዋል። አውደ ርዕዩም በአራት ትዕይንት የተከፈለ ሲሆን በተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች በደመቀ ሁኔታ እንደሚታጀብ ተገልጾል። በፊንላንድ እና በአጎራባች ሀገሮች አድባራት የምትገኙ ምእመናን የበዓሉ በረከት ተሳታፊ እንድትሆኑና በዕለቱም ዐውደ ርእዩን እንድትጉበኙ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በጻድቁ ስም ጥሪውን ያስተላልፋል። ወስብሐት......

Read More