ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል-ማዕዶት ማለት መሻገር, ማለፍ ማለት ነው. በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን , ከሞት ወደ ሕይወት, ከሲኦል ወደ ገነት, ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን.
✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል-በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ; ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል. ዮሐ. 20 27-29
✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል-በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን . ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ;. የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን
✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል-ዕለት ለአዳም የተሰጠው በዚህ ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን
✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል – በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል. . ስለ እርሷ ራሱን ክርስቶስ አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል
ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው;. ለሕንፃ አልሞተምና ክርስቶስ
✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል-በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል.
✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል-በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል .

ቅዱስ ቀን ይሁንላችሁ !!!

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *