በዕለተ ሆሣዕና ለምን ዘንባባ ይዘን እንዘምራለን?

by ግንኙነት ክፍል
1- ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔርን አመስግኖበታል (የደስታ መግለጫ በመሆኑ አንተ ደስታ የምትሰጥ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው)
2- ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
3- ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
4- ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
5- ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
6- ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው
አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡