ዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት

የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ሰንበት «ደብረ ዘይት» ተብሎ ይጠራል፡፡
ደብረ ዘይት ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ተራራው በዚህ ስም የሚጠራው ለዘይት የሚሆን የወይራ ተክል በብዛት ስለሚበቅልበት ነው፡፡ ጌታችን ቀን ሲያስተምር ውሎ በደብረ ዘይት ያድር ነበር፡፡ ለደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ በምሳሌ ያስተማረውን ይተረጉምላቸው ነበር፡፡ የዓለም ፍጻሜና የዳግም ምጽአቱን ምልክት ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማራቸው በዚሁ ተራራ ላይ ነውና የጌታን ዳግም ምጽአት የምናስብበት አምስተኛው የዐቢይ ጾም ሰንበት ስሙን ከተራራው ወስዷል ማለት ነው፡፡

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትቤት የሥነ ጽሁፍ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ
Share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *