ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

እግዚአብሔር አምላክ ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣው ከተፈጠረበት ሥርዓት ጋር ነው። የዓለም ተፈጥሮም ያለ ሥርዓት ትርጉም የለውም። ፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔርን ከሚያደንቅበት ነገር አንዱ የተሰጠውን ሥርዓት ጠብቆ መጓዙ ነው። ወንዞች ወደ ዝቅተኛ ስፍራ ይፈስሳሉ፣ አራዊት በሌሊት ይወጣሉ፣ ሰዎች ተግባራቸውን በቀን ያከናውናሉ፣ ፀሐይ በምሥራቅ ትወጣለች። ይህ ሁሉ የሚያስተምረን ሥርዓት ከጥንተ ፍጥረት ጀምሮ የነበረና ወደፊትም የሚቀጥል መሆኑን ነው። መዝ ፩፻፫፡ ፮-፳፭።

ሥርዓት ሠርዐ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ስም ነው። ትርጉሙም ደምብ አሠራር ማለት ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ስንል የቤተ ክርስቲያን መገልገያ ደንብ ማለታችን ነው። አምልኮተ እግዚአብሔር የሚከናወንባት ቤተ ክርስቲያን ምስጢራዊና መንፈሳዊ ሥርዓት አላት። መንፈሳዊ አገልግሎቷንም የምትፈጽምበት ደንብ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይባላል። ይህም ደንብ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየጊዜው በሲኖዶስ በመወሰን ለቤተ ክርስቲያን ያስረከቡት ነው። በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የዕለት ተዕለት ሥርዓተ አምልኮታቸውን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመመራት ያከናውናሉ። በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ከሚከናወኑት ውስጥ አንዱ ሥርዓተ ቅዳሴ ሲሆን የበዓላት አከባበርም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሥር ይጠቃለላል።

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን – ክፍል አንድ

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን – ክፍል ሁለት

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን – ክፍል ሶስት

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን – ክፍል አራት

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን – ክፍል አምስት

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን – ክፍል ስድስት

 

 

 

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *