የ2018 ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ

by ግንኙነት ክፍል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰሜን ምዕራብ አውሮፖ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የአጥቢያው ምእመናን በተገኙበት እሑድ ጥር 6 2010ዓ.ም. ወይም Jan 14.2018 በፑኪንማኪ የመሰባሰቢያ አዳራሽ እ.ኤ.አ. የ2018 ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ፡፡ በጉባኤው መጀመሪያ ላይ የ2017 የክፍሎች የዕቅድ አፈጻጸም እና፣ የሒሳብ ሪፖርት እንዲሁም የኦዲት ምርመራ ሪፖርቶች ለጉባኤው ቀርበዋል፡፡ ሪፖርቶቹ ከቀረቡ በኋላ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ለቀረቡ ጥያቄዎችም ከክፍል ተወካዮች እና ከደብሩ አስተዳዳሪ ምላሽ ተሰጥቶ ጉባኤው ሪፖርቶቹን አጽድቋል፡፡
በመቀጠልም እ.ኤ.አ. የ2018 በጀት ዓመት የክፍሎች ዕቅድ ለጉባኤው የቀረበ ሲሆን የቀረበውን ዕቅድ ተከትሎም ከተሳታፊዎች አስተያየት እና ማሳሰቢያ የተሰጠ ሲሆን በተለይ ሕፃናት የወደፊቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተረካቢዎች እንደመሆናቸው መጠን በሃይማኖት ትምህርት ተኮትኩተው እንዲያድጉ ወላጆች ከፍተኛ ክትትል በማድረግ የድርሻቸውን እንዲወጡ አጽንዖት በመስጠት ጉባኤው የቀረበውን ዕቅድ አጽድቋል፡፡
በመጨረሻም የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ ለሕዝቡ ባስተላለፉት መልእክት፣ ያታቀዱትን ዕቅዶች ለመፈጸም ሁሉም የደብሩ ምእመናን በሚችሉት አቅም ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም በአገልግሎት መደራረብ ምክንያት በአገልግዮች ላይ ከፍተኛ ጫና እናዳለ እና የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም ለጥቂት ሰዎች ብቻ የሚተው ተግባር ስላልሆነ ምእመናን በቅርብ ድጋፍ እና እገዛ በማድረግ በአገልግሎት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅረበው ጉባኤው በጸሎት ተዘግቷል፡፡
Recommended Posts

ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ
October 04, 2023

ሀገረ ስብከቱ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጠቅላላ ጉባኤውን አጠናቀቀ
September 03, 2023

በፊንላንድ ሀገር የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ተከናወነ !
September 03, 2023