የእርቀ ሰላሙን ሂደት የሚደግፍ የአቋም መግለጫ ወጣ

የእርቀ ሰላሙን ሂደት የሚደግፍ የአቋም መግለጫ ወጣ

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ በሁለቱ ሲኖዶሶች መሓከል የተጀመረውን እርቀ ሰላም እንደሚደግፍ አስታወቀ፡፡ እርቀ ሰላሙን በሚመለከት በወጣው ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ላይ እንደተጠቆመው የሁለቱ ሲኖዶሶች አባቶች እርቀ ሰላሙን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈጽሙ፣ ለእዚህም ሂደት የተቋቋመው አስተባባሪ ኮሚቴ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ደብሩ እንደሚደግፍ ተጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም፣ በአጥቢያው እና በውጭ አባቶች አስተዳደር ሥር ያሉ ማኅበረ ምእመናን እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን የእርቀ ሰላሙን ሂደት እንዲደግፉ እና ለእርቁ መሳካትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል፡፡

 

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *