የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ

የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል በድምቀት ተከበረ

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ሕዳር 12 ቀን የሚከበረው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ከትላንት በስትያ ከሄልሲንኪ ከተማ ተጉዘው በቦታው በተገኙ ኢትዮጵያውናን እና ኤርትራውናን ሕዳር 9 ቀን 2010 ዓ.ም በፊላንድ በድምቀት  ተክብሯል።

ከፊላንድ ዋና ከተማ ሄልሲንኪ 150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በቱርኩ ከተማ በሰማዕቱ በቅዱስ አሌክሳንደር የፊላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከማላዳው  ጀምሮ በቅዳሴ  የተጀመረው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ቀኑን ሙሉ የተለያዩ መንፈሳዊ መዝሙሮች እና ትምህርቶች ቀርበውበታል ።

በፊላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ የወንጌል ትምህርት ሰጥተዋል።የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት የሕፃናት  ክፍል መዝሙሮች እና ትምህርታዊ ጽሑፎችን ሲያቀርቡ  ዓበይት መዘምራንም  ለዕለቱ ያዘጋጁትን ወረብ  አቅርበዋል ።

በማያያዝም  በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ዲያቆናት እና ወንድሞች ለሕዝበ ክርስቲያኑ ቃለ እግዚአብሔርና ምክር  ተሰጥቶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖአል።

የቅዱስ ሚካኤል በዓል Nov 2017

 

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *