የፀሎተ ሐሙስ በዓል በቤተክርስቲያናችን ተከብሮ ዋለ

by ግንኙነት ክፍል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ የሚከናወነው የፀሎተ ሐሙስ የእግር አጠባ እና የጸሎተ ቅዳሴት ሥነ ሥርዓት ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ትህትናን ለደቀመዛሙርቱ ሐዋርያት ያስተማረበት ቀን መሆኑንና እንዲሁም በማግስቱ ዐርብ ስለ ሰዎች ሲል ስለሚቆረሰው ሥጋውና ስለሚፈሰው ደሙ ትምህርት ሰጥተዋል። በመቀጠልም አባታችን የምእመናንን እግር በማጠብ የሕፅበተ እግር ሥርዓትን አከናውነዋል፡፡ አምላካችን እራሱን ዝቅ አድርጎ ያስተማረንን ትህትና እኛ ልንተገብረው ይገባል ብለዋል፡፡ በማያያዝም ነገ ዕለተ ዐርብ የስቅለት በዓል ቀኑን ሙሉ እንደሚከናውን ተገልጿል።
ጸሎተ ሐሙስ 2016
ለብርሃነ ትንሣኤው ያድርሰን፡፡
Recommended Posts
በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የቅዱስ ዑራኤል ጽዋዕ ማኅበር ተመሠረተ።
March 11, 2023