የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት ከአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ጋር ለማክበር ዝግጅት መጨረሱን አስታወቀ

የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት ከአንድ ቀን  ዐውደ ርእይ ጋር ለማክበር ዝግጅት መጨረሱን አስታወቀ

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር ግንቦት 13/2008 ዓ.ም(May 21 2016) የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን በዓለ ፍልሠት እንደሚከበር የደብሩ ጽ/ቤት አስታወቀ። በዓሉ በደብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚከበር የተገለጸ ሲሆን በዕለቱ “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም አንተው” በሚል መሪ ቃል ልዩ የአንድ ቀን አውደ ርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያካሄድ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፍቃድ ገልጸዋል። አውደ ርዕዩም በአራት ትዕይንት የተከፈለ ሲሆን በተለያዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች በደመቀ ሁኔታ እንደሚታጀብ ተገልጾል።
በፊንላንድ እና በአጎራባች ሀገሮች አድባራት የምትገኙ ምእመናን የበዓሉ በረከት ተሳታፊ እንድትሆኑና በዕለቱም ዐውደ ርእዩን እንድትጉበኙ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በጻድቁ ስም ጥሪውን ያስተላልፋል።

ዕውደ ርእይ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *